መንግስት ያለ ፍላጎታችን ደሞዛችንን እየቆረጠብን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞች ተናገሩ። (አሻራ፣ጥር፣14፣2013 ዓ•ም ባህርዳር) መንግስት ገበታ ለሀገር በሚል ፕሮጅክ…

መንግስት ያለ ፍላጎታችን ደሞዛችንን እየቆረጠብን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞች ተናገሩ። (አሻራ፣ጥር፣14፣2013 ዓ•ም ባህርዳር) መንግስት ገበታ ለሀገር በሚል ፕሮጅክት ስም ያለፍላጎታችን ደሞዛችንን እየቆረጠብን ነው ሲሉ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ድስትሪክት ሰራተኞች ለአሻራ ሚዲያ ገለፁ። ሰራተኞቹ ከዚህ ቀደም ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ለማዋጣት ፍቃደኛ የሆናችሁ ፈርሙ በሚል በየ ቅርንጫፉ ፎርም እየዞረ እንደነበር ገልፀዋል።ነገር ግን ፎርሙ ላይ ያልፈረምነውንም ሰዎች ጭምር ከደሞዛችን ለሁለት (2) ዓመት የሚቆይ ከ500-700 ብር ድረስ ተቆርጦብናል ብለዋል ቅሬታ አቅራቢወቹ። #አሻራ በዩዩቲዩብ ያገኙናልhttps://www.youtube.com/c/AMNMedia በቴሌግራም ያግኙን https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply