መንግስት ያልተጣራ እና የተዛባ መረጃ ከመስጠት እንዲቆጠብ ተመከረ፡፡          አሻራ ሚዲያ    ታህሳስ 9/2013 ዓ•ም ባህርዳር በባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስት…

መንግስት ያልተጣራ እና የተዛባ መረጃ ከመስጠት እንዲቆጠብ ተመከረ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 9/2013 ዓ•ም ባህርዳር በባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስት…

መንግስት ያልተጣራ እና የተዛባ መረጃ ከመስጠት እንዲቆጠብ ተመከረ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 9/2013 ዓ•ም ባህርዳር በባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ፊት ቀርበው የህወሓት አመራሮች ሀገረ ሰላም ላይ ናቸው ብለው ነበር፡፡ እየተከታተልናቸው ቢሆንም፣ ንፅሃንን ላለማጥቃት በከበባ ውስጥ አስገብተናቸዋል ብለው ነበር፡፡ በወቅቱ የህወሓት አመራሮች ሙሉ በሙሉ በመንግስት እይታ ስር እንዳሉ የተገለፀ ቢሆንም፣ዛሬ ደግሞ ያሉበትን የጠቆመ 10 ሚሊየን ሽልማት ይሰጠዋል ይላል፡፡ ባለፈው ከታዩ እና ከበባ ውስጥ ከገቡ ከየት ተሰውረው እንደበረሩ ግልፅ አይደለም፡፡ ከዚህ በፊትም የህወኃት ሮኬት ተደብድቧል ተብሎ ዜና እንደታወጀ ፣ እንደገና ህወኃት 16 የሚደርሱ ሮኬቶች ወደ ባህርዳር፣ጎንደር እና አስመራ አስወንጭፏል፡፡ ይህም ለጥንቃቄ እና ለትግል አስቸጋሪ ሲሆን ተስተውሏል፡፡ሀሳባቸውን ለአሻራ ያካፈሉ ግለሰቦች እንደሚሉት መንግስት የተናበበ፣ሚዛን የሚደፋ እና ምክንያታዊ የሆነ መረጃ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡ ኦነግ እና የቢሻንጉል ጉምዝ ሽፍቶች ተደመሰሱ እየተባለ የሚሰጠው መግለጫም ሚዛን የሚደፋ አልሆነም፡፡ መንግስት የህዝብን ልብ ለመግዛት የሚሰጠው የተሳከረ መረጃ ለዜጎች አስቸጋሪ ሁኔታን እየፈጠረ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply