You are currently viewing መንግስት ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬን በአስቸኳይ እንዲፈታ ብሎም የፕሬስ አባላትን ማሰሩን እንዲያቆም የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ( ሲፒጄ) ጥሪ አደረገ። አማራ ሚ…

መንግስት ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬን በአስቸኳይ እንዲፈታ ብሎም የፕሬስ አባላትን ማሰሩን እንዲያቆም የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ( ሲፒጄ) ጥሪ አደረገ። አማራ ሚ…

መንግስት ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬን በአስቸኳይ እንዲፈታ ብሎም የፕሬስ አባላትን ማሰሩን እንዲያቆም የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ( ሲፒጄ) ጥሪ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የፌደራል ፖሊስ አባላት የዩቲዩብ የግል ንብረት የሆነው ሮሃ ኒውስ የዜና ማሰራጫ መስራች እና ዋና አዘጋጅ አራጋው ሲሳይን በቁጥጥር ስር ስለማዋላቸው ጠበቃ አዲሱ አልጋው እና ባለቤታቸው ህይወት መና ለሲፒጄ ስለመግለጻቸው ተወስቷል። በተመሳሳይ የአማራ ድምጽ የስርጭት ዋና አዘጋጅ ጌትነት አሻግሬ በአዲስ አበባ ከመኖሪያ ቤቱ እያለ ተወስዶ ስለመታሰሩ ጠበቃ አዲሱ አልጋው እና የጋዜጠኛው እህት እመቤት ታደሰ ሲፒጄን በስልክ አነጋግረዋል። ሁለቱም ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ አራዳ ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሰሞኑ ቀርበው ፖሊስ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሁከትና ብጥብጥ ቅስቀሳ አድርገዋል በሚል ክስ እንደመሰረተባቸው ሲፒጄ አመላክቷል። “ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ጌትነት አሻግሬ እና አራጋው ሲሳይ በአስቸኳይ መፈታት አለባቸው እና ከስራቸው ጋር በተያያዘም ተጨማሪ እንግልት እንዳይደርስባቸው ማረጋገጥ አለባቸው” ሲል የCPJ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ አንጀላ ኩንታል ተናግረዋል። “ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች በየጊዜው በሚደርሰው የእስር ዛቻ ውስጥ መሥራት የለባቸውም። ይህ ወሳኝ ጋዜጠኞችን ከእስር ቤት የመወርወር ዘዴ መቆም አለበት።” የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል። የሮሃ ኒውስ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና የአማራ ድምጽ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ:_ መጋቢት 17/2015 በፌደራል ፖሊስ ከመኖሪያ ቤታቸው መያዛቸው፣ መጋቢት 19/2015 ፍ/ቤት መቅረባቸው እና ለሚያዚያ 2/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጣቸው መሆኑ፣ መጋቢት 20/2015 ቤታቸው በፖሊስ መፈተሹ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply