መንግስት ጥቅማችን ተነካ በሚል በኢትዮጵያ ህልውና ላይ በመጣው የህወሓት ቡድን ላይ የጀመረውን ጥቃት በጥንቃቄ እንዲያስኬድ ኦነግ አሳሰበ።

ህወሃት ይህችን ሀገር በጦርነት መልሰን እንይዛለን ብሎ ማሰቢ የተሳሳተ ውሳኔ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መንግስት ጉዳዩንበጥንቃቄ መያዝ እንዳለበትም ኦነግ አሳስቧል፡፡

ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ የነበራቸው አቶ ቀጀላ መርዳሳ አሁንም ቢሆን ችግሮን በህጋዊ እና በህገ መንግስታዊ መንድ ለመፍታት ከህውሓት ፍቃደኝነት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊትም መንግስት ነገሮችን በሆደ ሰፊነት ለማለፍ ሲለፋ እንደነበር እናውቃለን ያሉት አቶ ቀጀላ አሁንም ቢሆን አንዳንዶቹ ግን በቶሉ መልስ ሊሰጣቸው ይገባ እንደነበርም አንስተዋል፡፡

አሁንም ቢሆን ከጦርነት በኃላ ሊከሰት የሚችል ቀውስን ለመከላከል ይቻል ዘንድ ይህ ጉዳይ በመንግስት ብቻ መያዝ አለበት የሚል አቋም አለን ብለዋል፡፡

ማዕከላዊ መንግስቱ ላይ ያነጣጠረና ትኩረቱን እና ሀይሉን ሊከፋፍል ያሰበ ጦርነት ለሆን ስለሚችል የኢትዮጲያ ህዝብ በዘር ፤ሀይማኖት ሳይለይ ሀገር እንዳይፈርስ ሁሉም በንቃት አከባቢውን መጠበቅ እንዳለበት ገልጻዋል፡፡

ይህ አይነቱ ዘመቻ በምንም መልኩ በትግራይ ያለውን ህዝብ የሚጎዳ እንዳይሆንም ጥንቃቂ ማድረግ እንደሚያስፈልገውም አቶ ቀጀላ ተናግረዋል።

ዋናው የዘመቻው ኢላማ ጥቅማችን ተነካ የሚሉ ጥቂት ቡድኑች ናቸው ፡፡ ይህንን ጉዳይ ከትግራይ ህዝብ ጋር መቀየጥ አያስፈልግም ሲሉ ሀሳባቸውን ነግረውናል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply