መንግስት ጥያቄ ከሚነሳባቸው አወዛጋቢ ቦታዎች ታጣቂዎችን ለማንሳት እየሰራሁ ነው አለ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እንደገለፁት «አወዛጋቢ ቦታዎች»ባሏቸው እና ጥያቄ…

መንግስት ጥያቄ ከሚነሳባቸው አወዛጋቢ ቦታዎች ታጣቂዎችን ለማንሳት እየሰራሁ ነው አለ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እንደገለፁት «አወዛጋቢ ቦታዎች»ባሏቸው እና ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ከፌደራል መንግስት ውጭ የሆኑ ታጣቂዎችን የማስወጣት እየሰራ ነው ።

በጦርነቱ የተፈናቀሉትንም ወደቀዬአቸው ለመመለስ የፌደራሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ የእስካሁን በተያዘለት ግዜ ባይሳካም፥ ጥረቶች መቀጠላቸውንም አንስተዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ አያይዘውም በኤርትራ ሰራዊት የተያዙ ቀሪ አካባቢዎች ለመለየት እና መፍትሔ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑ ገልፀዋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ በዚህ ሳምንት የአፍሪካ ሕብረት ተወካዮች በተገኙበት፥ በፕሪቶሪያው ውል አፈፃፀም ዙርያ ውይይት ለማድረግ ዕቅድ መያዙን የትግራይ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ገልጿል።

በውይይቱም በተለይም ባልተፈፀሙ የስምምነቱ ነጥቦች ላይ ምክክር እንደሚደረግ የትግራይ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሐላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም ለዶቼቬለ ገልፀዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply