You are currently viewing መከላከያ ሀገሪቱን ለመታደግ እየወሰደው ያለውን ዕርምጃ የጋምቤላ የክልል እንደሚደግፍ አቶ ዑሞድ ኡጁሉ አስታወቁ

መከላከያ ሀገሪቱን ለመታደግ እየወሰደው ያለውን ዕርምጃ የጋምቤላ የክልል እንደሚደግፍ አቶ ዑሞድ ኡጁሉ አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ሀገሪቱን ለመታደግ እየወሰደው ያለውን ዕርምጃ የጋምቤላ የክልል እንደሚደግፍ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዑሞድ ኡጁሉ አስታወቁ።

ሕወሓት በሠራዊቱ ላይ ያደረሰው ጥቃት የሀገር ክህደት ወንጀል መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል፡፡

ይህ ድርጊትም በፅኑ ሊኮንን ይገባዋል ያሉት አቶ ዑሞድ፤ የፌዴራል መንግሥት በሕወሓት ላይ የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ አጠናከሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በጋምቤላ ክልል ያሉ የፀጥታ አካላት የሕዝብን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት እንዲወጡም መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ ሕዝቡም ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን ሰላሙን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

The post መከላከያ ሀገሪቱን ለመታደግ እየወሰደው ያለውን ዕርምጃ የጋምቤላ የክልል እንደሚደግፍ አቶ ዑሞድ ኡጁሉ አስታወቁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply