መከላከያ ሠራዊት ለመጨረሻው ምዕራፍ ትዕዛዝ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 3013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግሥት ለሕወሓት አመራሮችና…

መከላከያ ሠራዊት ለመጨረሻው ምዕራፍ ትዕዛዝ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 3013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግሥት ለሕወሓት አመራሮችና ታጣቂዎች የሰጠውን የ72 ሰዓት እጅ መስጠት ማስጠንቀቂያ ተከትሎ መቀሌ ከተማን የከበበው የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለሦስተኛውና ለመጨረሻው ምዕራፍ በተጠንቀቅ ቆሞ ትዕዛዝ በመጠባበቅ ላይ መሆኑን አስታውቋል። ‹‹የሕወሓት የጥፋት ኃይል ያሰበው ሴራ እየከሸፈበት ነው፡፡ አሁን ደግሞ አዲስ የጥፋት ዕቅድ ማውጣቱን ደርሰንበታል፤›› ብለዋል፡፡ ይህንንም ድርጊት ለመፈጸም ልዩ ገዳይ ቡድን ማቋቋሙን ጠቁመዋል፡፡ እሑድ ኅዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት፣ በትግራይ ክልል የተጀመረው የሕግ ማስከበር ሁለተኛው ምዕራፍ መጠናቀቁንና የሕወሓት አመራሮች በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ የ72 ሰዓት መሰጠቱን ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡ የአገር መከላከያ ሠራዊት የሁለተኛውን ምዕራፍ መቋጯ ያደረገው መቀሌ ከተማን በ50 ኪሎ ሜትር ከበባ ውስጥ በማድረግ መሆኑ ታውቋል፡፡ ሠራዊቱ በዳንሻ፣ በሑመራ፣ በሽሬ፣ በሽራሮ፣ በአክሱም፣ በአድዋ፣ በአዲግራት፣ በአላማጣ፣ በጨርጨር፣ በመሆኒ፣ በኮረምና በሌሎችም ቦታዎች በወሰደው ዕርምጃ ሕዝብ እየታደገና ድል እያደረገ መቀሌ ዙሪያ መድረሱ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ከመንግሥት ጎን በመሆን፣ የሕወሓት አመራሮችን ለፍርድ ለማቅረብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጋር በጽሑፍ መልዕክት አቋማቸውን ማስታወቃቸው የተገለጸው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ እጅ መስጠት አይሞከርም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ሪፓርተር

Source: Link to the Post

Leave a Reply