
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል በፋኖ ስም በሚንቀሳቀሱ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ሸኔ በተሰኘው ታጣቂ ኃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገለጸ። ባለፉት ዓመታት መንግሥት ሸኔ የሚለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ክፍሎች ግጭቶች ውስጥ የቆየ ሲሆን፣ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነትን ማብቃት ተከትሎ በአማራ ክልልም ተመሳሳይ ግጭቶች እያጋጠሙ መሆናቸው ሲዘገብ ቆይቷል።
Source: Link to the Post