መከላከያ ሰራዊት ላይ የጽንፈኛው ሃይል የአገር ክህደት ተግባር መፈጸሙን የጁንታው አባል መሰከሩ

መከላከያ ሰራዊት ላይ የጽንፈኛው ሃይል የአገር ክህደት ተግባር መፈጸሙን የጁንታው አባል መሰከሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ሰራዊት ላይ የጽንፈኛው ሃይል የአገር ክህደት ተግባርና ጥቃት ማድረሱን የጁንታው አባል የሆኑት ሴኮቱሬ ጌታቸው መሰከሩ።
የሕወሓት ጽንፈኛ ቡድን ሚዲያ በሆነው ድምጸ ወያነ የጁንታው ቡድን አባላት በአገር ላይ የፈጸሙትን ክህደት ሲናገሩ ተደምጠዋል።
በዚህም የጽንፈኛው ቡድን አባል የሆኑት ሴኮቱሬ ጌታቸው የጁንታው ጽንፈኛ ሃይል በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባላት ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን መስክረዋል።
በዚህም የአገር መከታ በሆኑ የሰራዊቱ አባላት ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ነው የመሰከሩት።
የጽንፈኛው ሃይል በሰራዊቱ ስር የነበረውን የጦር መሳሪያ ለመዝረፍ መሞከሩንም ተናግረዋል።
የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ የጁንታ ህወሃት ቡድን ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው መካከል አቶ ሴኩቱሬ በተራ ቁጥር 63 የሚገኙ መሆናቸው ይታወቃል።
የህወሃት ጁንታ ቡድን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን ይህንን ተከትሎ መንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻ ማካሄድ ጀምሯል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post መከላከያ ሰራዊት ላይ የጽንፈኛው ሃይል የአገር ክህደት ተግባር መፈጸሙን የጁንታው አባል መሰከሩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply