መከላከያ ሰራዊት አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮች መደምሰሳቸውን አሳወቀ።የተደመሰሱት አመራሮች ፦1. አቶ ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም…

መከላከያ ሰራዊት አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮች መደምሰሳቸውን አሳወቀ።

የተደመሰሱት አመራሮች ፦

1. አቶ ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም ውጊያውን የመሩና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዙ፣ በመጨረሻም በሰራዊቱ ላይ ውጊያ እንዲከፈት ትዕዛዝ የሰጡ፣

2. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

3. አቶ አባይ ፀሃዬ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ ከመከላከያ የከዱ ከነጥበቃዎቻቸው ተደምስሰዋል።

በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች ፦

1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዱ
2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረ
5. አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበረ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብ/ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፣ አሁንም የተደበቁ የህወሓት ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ:ኢዜአ

Source: Link to the Post

Leave a Reply