#መዋሸት ከአዕምሮ ጤና ችግር ጋር ምን ያገናኘዋል ?መዋሸት ከልጅነት ዕድሜ ይጀምር እና እስከ እድሜ አመሻሽ ድረስ ሊቀጥል እንደሚችልም ይነገራል። ውሸት የህመም ምልክት ሊሆን እና የስብዕና…

#መዋሸት ከአዕምሮ ጤና ችግር ጋር ምን ያገናኘዋል ?

መዋሸት ከልጅነት ዕድሜ ይጀምር እና እስከ እድሜ አመሻሽ ድረስ ሊቀጥል እንደሚችልም ይነገራል።
ውሸት የህመም ምልክት ሊሆን እና የስብዕና መለያ ተደርጎ ይታሰባል፡፡

ለውሸት ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችን እና የመፍትሄ ሃሳችን በተመለከተ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት የአእምሮ ሀኪም የሆኑት ዶክተር እስጢፋኖስ እንዳላማው ውሸትን ህመም ነው ማለት ባይቻልም ሲደጋገም ግን እንደ ህመም ባይወሰድም የህመም ምልክት ግን ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ውስጥ ሊዋሹ የሚችሉ ሲሆን፤ ጊዜ እና ቦታ እየመረጡ የሚዋሹ እና በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ መዋሸትን የሚመርጡ በማለት ዋሾዎችን በሁለት መልኩ ከፍሎ መመልከት እንደሚቻል ይገለጻል፡፡

#ለመዋሸት እንደ ምክንያት የሚነገሩ መላምቶች

• የአእምሮ ጭንቀት
• የጤና እክል
• ዝቅተኛ በራስ መተማን
• በሰዎች ዘንድ ተፈላጊነትን ለመጨመር በማሰብ
• የናርስሲሲት ስብዕና ያላቸው ሰዎች (አፍቅሮ ራስ)
• ከዚህ በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ የሚዋሽ ሰው ካለ ህጻናት ውሸትን እየተለማዱ እንዲያድጉ ያደርጋል፡፡

በመዋሸት ሌሎች ለመጉዳት የሚሞክሩ ሰዎች ቢኖሩም እንኳን ያለፈ የህይወት ታሪካቸው በሚያሳድርባቸው አሉታዊ ተጽዕኖ ብቻ ሰዎች ሊዋሹ ይችላሉ ተብሏል፡፡ አንዳንዶች ለምን እንደሚዋሹ ምክንያቱን ባይቁትም ፍላጎታቸው መዋሸት ብቻ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ፡፡

የመዋሸት ፍላጎታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ይጨምር እና በመዋሸታቸው ደስተኛ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ሲናገሩም እንደሚስተዋል ተነግሯል፡፡ ሰዎችን ያለ ምክንያት ማታለል፣ አመለካከታቸውን ማሳት የስብዕና እክል ተደርጎ ይታሰባል፡፡

በህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ጉዳቶች ሰዎች እንዲዋሹ እንደ ምክንያትም የሚነሳ ሲሆን ፍርኃትም ለመዋሸት ምክምያት ሊሆን እንደሚችል ተመላክቷል፡፡ ሆን ብሎ መዋሸት፣ ሀላፊነትን አለመውሰድ፣ እንደ ታመሙ ማስመሰል፣ ግልፍተኛ መሆን እና የሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ በሚዋሹ ሰዎች ይስተዋላል ተብሏል፡፡

#እንዴት መዋሸትን ማቆም ይቻላል፤

በሰዎች እንዋሻለን የሚለው አመለካከት አለመሩ ለሚዋሹ ሰዎች በስነ ልቦና ባለሞያ የሚደረግላቸውን ህክምና አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ተነግሯል፡፡

ሰዎች በቅድሚያ ስለ ውሸት እራሳቸውን መጠየቅ እንደሚገባቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በንግግር ህክምና የመዋሸት ባህሪን ማከም ይቻላልም ተብሏል፡፡

በህክምናው ሰዎች የሚዋሹበትን ምክንያት እንዲረዱ ማድረግ እና ሌሎች ተጓደኝ የአእምሮ ህመሞችን ካሉ ማከምን ያካተተ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply