መደበኛ የቀዶ ጥገና ስራ የጀመረው የዶክተር አምባቸው መኮንን የጠገዴ ቅራቅር የመጀመሪያ ደረጃ የመታሰቢያ ሆስፒታል ያሉበት የግብአት ጉድለቶች እንዲሟሉለት ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

መደበኛ የቀዶ ጥገና ስራ የጀመረው የዶክተር አምባቸው መኮንን የጠገዴ ቅራቅር የመጀመሪያ ደረጃ የመታሰቢያ ሆስፒታል ያሉበት የግብአት ጉድለቶች እንዲሟሉለት ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

መደበኛ የቀዶ ጥገና ስራ የጀመረው የዶክተር አምባቸው መኮንን የጠገዴ ቅራቅር የመጀመሪያ ደረጃ የመታሰቢያ ሆስፒታል ያሉበት የግብአት ጉድለቶች እንዲሟሉለት ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር በቆየ ምትኩ እንደተናገሩት የጠገዴ ቅራቅር የመጀመሪያ ደረጃ የመታሰቢያ ሆስፒታል ስራ ከጀመረ ሶስት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በተለይ የተመላላሽ ህክምና፣የተኝቶ ህክምና ፣የእናቶችና ህፃናት ህክምና እንዲሁም የመለስተኛ ቀዶ ጥገና የህክምና አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በሆስፒታሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከጀመሩ አገልግሎቶች መካከል አንዱ የመደበኛ ቀዶ ጥገና አገልግሎት ሲሆን ከአሁን በፊት በተለያዩ ምክንያቶች ሳይጀምር እንደቆየና ብዙ ታካሚዎች ሪፈር እየተባሉ ወደተለያዩ የህክምና ተቋማት እየተላኩ ለተጨማሪ ወጪ ሲዳረጉ እንደነበር አውስተዋል። አሁን ግን ችግሮቹ ሙሉ በሙሉ ተፈተዋል ባይባልም በተቻለ መጠን ክፍተቶችን በመሙላት መደበኛ የሆነ የቀዶ ጥገና አገልግሎት ስራ ማስጀመር የተቻለ መሆኑን ለማህበረሰቡና ለእናቶች ኮንፈረንስ በማድረግ እውቅና መፍጠር እንደተቻለና ሁሉም ማህበረሰብ እየመጣ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ዶ/ር በቆየ ተናግረዋል። በሆስፒታሉ የድንገተኛ የማህፀንና የፅንስ ቀዶ ጥገና ባለሙያ የሆኑት ኖሀሚን ዳኘው እንደሚናገሩት ከሆስፒታሉ ከተቀጠሩ አንድ ዓመትና ከዚያ በላይ ቢሆናቸውም ለሆስፒታሉ የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት፣ የደም ባንክና የመሳሰሉ ለተሟላ የቀዶ ጥገና አገልግሎት መስጫ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ባለመሟላታቸው መደበኛ ስራ ሳይጀመር ቆይቶ ነበር ብለዋል። አሁን ግን ችግሮች ሙሉ በሙሉ ባይፈቱም ከጎንደር የደም ባንክ አገልግሎት ጋር በመነጋገር የቅራቅር ጤና ጣቢያ የመብራት ችግር ስለሌለበት የደም ባንኩን ከዚያው በማስቀመጥ የሚፈልገውን የደም መጠን እያስመጡና ሆስፒታሉ ባለው የጀነሬተር መብራት እየታገዙ አገልግሎቱን እንጀመሩ ተናግረዋል። ባለሙያዋ አክለው እንደተናገሩት እስካሁን ድረስ ሶስት የወሊድና አንድ መደበኛ ቀዶ ጥገና በድምሩ አራት ውጤታማ የሆነ የተሳካ የቀዶ ጥገና አገልግሎት እንደሰጡና ወደ ሆስፒታሉ ሪፈር እየተፃፈላቸው የሚመጡ ተገልጋዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጧል። ለቀጣይም በሆስፒታሉ የተሟላ የቀዶ ጥገና አገልግሎት ለመስጠት የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት ተስተካክሎ የደም ባንኩ ከሆስፒታሉ እንዲቀመጥ ቢደረግ ፣የቀዶ ጥገና ክፍሉ የውሀ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽንና ሌሎች ክፍተቶች ያሉበት በመሆኑ እነዚህ ችግሮች የሚመለከተው አካል እንዲስተካከሉ የሚደረጉበትን ሁኔታዎች ሊያመቻች ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ካሁን በፊት እናቶች በገጠር ባህል ሲወልዱ ከፍተኛ የደም መፍሰስ፣ሌሎች ተጓዳኝ ህመሞችና በወሊድ ምክንያት ለሞት ይዳረጉ እንደነበርና በሆስፒታል መውለድ ለህፃኑም ሆነ ለወላድ እናቶች የተሻለ መሆኑን በሆስፒታሉ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸው ልጆቻቸውን የተገላገሉትና በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙት ወ/ሮ አታላ ባህታና ወ/ሮ አረጋሽ አያልነህ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የነርሲንግ ሚድዋይፍሪ አስተባባሪ የሆኑት አንዷለም ካሳው በበኩላቸው እስካሁን ድረስ በሆስፒታሉ የታካሚ ፍሰት አነስተኛ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ሆስፒታሉ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋፋት ላይ በመሆኑ በተለይ የተኝቶ ህክምና የምግብ አገልግሎት፣በክፍል ጥበት ምክንያት እስካሁን አገልግሎት ያልጀመሩ እንደ የፀረ ኤች አይ መድሀኒት፣የህፃናት ክትባት፣የቲቪ ህክምናና የመሳሰሉትን ለማስጀመር ሲባል ለጊዜውም ቢሆን ቆርቆሮ በቆርቆ የሆነ ክፍል ተሰርቶ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ ከሚመለከታቸው የወረዳ አመራሮችና አጋር አካላት ጋር በመነጋገር ችግሮቹን ለመፍታት ጥረት ቢደረግ መልካም ነው ብለዋል። በቀዶ ጥገና ክፍል የሰመመን ባለሙያ የሆኑት አማኑኤል አሻግሬ እንደሚሉት ለቀጣይ በሆስፒታሉ ደረጃውን የጠበቀ የቀዶ ጥገና አገልግሎት ለመስጠት ሲባል የሞኒተሪንግ ማሽን ፣የEcGገመዶችና የመሳሰሉ የቀዶ ጥገና ክፍል ቁሳቁሶች በብዛት የሲስተም ችግር ያለባቸው በመሆኑ ማሽኖቹ በባለሙያ እንዲስተካከሉ ወይም እንዲቀየሩ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል። የጠገዴ ወረዳ ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply