
መጋቤ ብርሃናት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ በጸጥታ አካላት ተይዘው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ ይገኛሉ። የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ የሆኑት መጋቤ ብርሃናት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከቤታቸው ወደ ሥራ ብለው ከወጡ በኋላ ሥልካቸው የተዘጋ እና መገኘት ያልቻሉ ሲሆን ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በኋላ ግን በጸጥታ አካላት ተይዘው ወደ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መወሰዳቸውን የዝግጅት ክፍላችን ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ችሏል። በተመሳሳይ መ/ር ተሾመ በየነ ገላን አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል። ምንጭ ማህበረ ቅዱሳን
Source: Link to the Post