You are currently viewing መግለጫ:- በአዲስ አበባ ላይ ያንዣበበውን የጅምላ አማራ ዘር ፍጅት ለማስቆም አማራ የሚመራው አስተዳደር በአዲስ አበባ ምስረታ አስፈላጊነት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አሊ እና ፓርቲያቸው…

መግለጫ:- በአዲስ አበባ ላይ ያንዣበበውን የጅምላ አማራ ዘር ፍጅት ለማስቆም አማራ የሚመራው አስተዳደር በአዲስ አበባ ምስረታ አስፈላጊነት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አሊ እና ፓርቲያቸው…

መግለጫ:- በአዲስ አበባ ላይ ያንዣበበውን የጅምላ አማራ ዘር ፍጅት ለማስቆም አማራ የሚመራው አስተዳደር በአዲስ አበባ ምስረታ አስፈላጊነት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አሊ እና ፓርቲያቸው የኦሮሞ ብልጽግና ወደ ስልጣን ከመጡበት 2010 ዓ.ም… ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰው ዘር ፍጅት፣ ዘር ማጽዳትና ሁሉን አቀፍ በደል ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እንደ ጎርጎሮሳዊያን አቆጣጠር በ2022 ብቻ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በሺመልስ አብዲሳ በሚመራው የኦሮሞ ክልል የጸጥታ ሃይሎችና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ሰራዊት (ኦነግ-ሸኔ) ሲገደሉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አማራዎች ከምዕራብ ኦሮሞ ዞኖች ተፈናቅለዋል፡፡ የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) በስፋት እየተካሄደ ያለውን የዘር ፍጅትና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ለመግታት እንደሚረዳ በመገንዘብ ጠቅላይ ሚንስትር አብይና ፕሬዚደንት ሺመልስ ከስልጣን እንዲነሱ ተደጋጋሚ ጥሪዎችን አድርጓል፡፡ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ከተቀዳሚ አላማዎቹ አንዱ አዲስ አበባ ከተማን ሙሉ በሙሉ ወደ ኦሮሞ ክልል መጠቅለል ነው፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት አማራዎች ስብሰባ፣ ሰላማዊ ሰልፍና ተቃውሞ ማድረግ አለመቻል፤ ዘርን መሰረት ያደረገእስር፣ ድብደባ እና ኦስገድዶ መሰወርን ጨምሮ የፖለቲካና ሲቪል መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡ የመብት ጥሰቱ የከተማዋን ባህላዊና ትምህርታዊ ምልክቶችን ኦሮሞ የማድረግ አፈጻጸም እያፋጠነው ሲሆን የከተማዋን ምልክቶች ኦሮሞ ከማድረግ እንቅስቃሴዎች መካከል፡- በአዲስ አበባ ከተማ ዳርቻዎች አዲስ በተመሰረተው ሸገር ከተማ አስተዳደር አማካኝነት ኦሮሞ ባልሆኑ ዜጎች ላይ የዘር ማጽዳት የኢትዮጵያን ሰንድቅ አላማ ማውልብልብ ማገድ ፥ የኢትዮጵያን ታሪክ ምልክቶች ማገድ በመንግስት ትምህርት ቤቶች የኦሮሞ ክልልን ሰንደቅ አላማና መዝሙር፣ ኦሮምኛ ቋንቋና የተዛባ ታሪክ በሃይል መጫን በጸጥታ ሀይል መዋቅሩ የኦሮሞ ተወላጆች ብልጫ ማስፈን በሺመልስ አብዲሳ እንደታመነው ታሪካዊና ባህላዊ ቦታዎችን ስያሜ መቀየር የዓድዋ ድል በዓል ማክበርን ጨምሮ የህዝብ ሁነቶችን መከልከል በቀድሞ ጊዜ በኦሮሞ ክልል ሲከበር የነበረውን ኢሬቻን ጨምሮ የኦሮሞ በዓላትን ወደ አዲስ አበባ ማምጣትና በዓላቱን ለአማራ ዘር ማጽዳትና ጭቆና ጥሪ ፥ የሺመልስ አብዲሳ የጥላቻ ንግግር ማስተላለፊያነት መጠቀምይገኝበታል። አማራን አናሳ ለማድረግና አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ወደ ኦሮሞ ክልል ለመጠቅለል በሚደረግ ጥረት የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ መሰረታዊ የህዝብ አሰፋፈር ለውጥ (ዴሞግራፊክ ኢንጂነሪንግ) እየፈጸመ ይገኛል፡፡ በወቅቱ የኦሮሞ ክልል ፕሬዚደንት ለማ መገርሳ በግልጽ እንደተናገረው በአዲስ ኣበባ የህዝብ ስብጥርን ለመቀየር የተገለጠ ሀሳብና አላማ በመያዝ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ አርሶ አደሮችን ከሶማሌ ክልልና ከኦሮሞ ክልል ድንበር አካባቢዎች በማምጣት በከተማዋ እንዲሰፍሩ ተደርጓል፡፡ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ በብዙ አጋጣሚዎች በአማራ ክልል የሚኖሩ አማራዎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከሉን ያመነ ሲሆን ክልከላው አሁንም ቀጥሏል፡፡ ተመሳሳይ ዘመቻዎች በሌሎች ታሪካዊ የአማራ ግዛቶች (ደራ፣ ናዝሬት፣ደብረዘይት እና ወለጋ) ተካሂዷል፡፡ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ በአሁኑ ወቅት ወደ አማራ ክልል እንዲፈናቀሉ ግልጽ አላማ በመያዝ በዋናነት አማራ የሆኑ ዜጎችን ቤት የማፍረስ ዘመቻ እያስፈጸመ ይገኛል፡፡ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲና ኦነግ በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ጥላቻ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ዘይቤ የሚመሩና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሱናቸው፡፡ በአዲስ አበባ የአድዋድል በዓልን አስመልክቶ የደረሰው ጥቃት እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የቀጠለው ጥቃት የኢትዮጵዊነትን ገመድ ለመበጠስና ራሷን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የመጨረሻው እርምጃ ነው፡፡ አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቤት ሆንም በታሪክና የህዝብ ስብጥር ግን የአማራ ከተማ ናት፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ በከተማዋ የአማራና ሌሎች ከኦሮሞ ውጭ ያሉ ማህበረሰቦች ህልውና አደጋ ላይ የወደቀ ሲሆን በወለጋ እየተፈፀመ ያለው የአማራ ዘር ፍጅት በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ሊፈፀም እንደሚችል ምልክት መታየት ጀምሯል:: ይህን ወሳኝ ምዕራፍ ከግምት ውስጥ በማስገባት በተለይም በአዲስ አበባ ላይ ያንዣበበውን የጅምላ ዘር ፍጅት ለማስቆም የዘር ፍጅቱ አሳቢ ፣ ፈፃሚ እና አስፈፃሚ የሆነው ኦነጋዊዉ የብልፅግና ቡድን ከስልጣኑ ታግዶ የከተማዋ ታሪካዊ ባለርስት እና በቁጥር አብዝኛው (majority) የሆነው አማራ የሚምራው አስተዳድር እንዲመስራት እና ወደ አማራ ክልል እንዲካለል ማህበራችን ይጠይቃል:: አማራ ክልል ኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛው ያልተማከለና በእውነተኛ ፌደራላዊ ስርዓት የሚተዳደር ሲሆን ብዝሃነትን የሚያከብርና የሚያበረታታ ክልል ነው፡፡ ስለዚህ በአዲስ አበባ የአማራ አስተዳደር በከተማዋ የአማራ ዘር ፍጅት ለመከላከል ብቸኛው መንገድ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከአማራ ውጭ ያሉ አናሳ ማህበረሰቦችም መብቶች መከበራቸውን ለማረጋገጥ ያግዛል፡፡ የአማራ ማኅበር በአሜሪካ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን ላይ የሚደርሰውን የሰብአዊ መብት ረገጣና ጭቆና አጣርቶ የሚያቀርብ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው። የአማራ ማኅበር በአሜሪካ ከሚመለከታቸው መንግስታት እና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን የአማራን ህዝብ በመወከል እየደረሰ ያለውን የአማራ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማስቆም እናአጥፊዎችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ይሰራል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply