መግለጫ እንዳይሰጥ ተከለከለ

ማክሰኞ ጷግሜ 1 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከሠላሳ በላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዛሬ ጷጉሜ 1 ቀን 2014 ከረፋዱ 3፡30 ጀምሮ ሊሰጡት የነበረው ‹የአስቸኳይ የሰላም ጥሪ› መግለጫ እንዳይሰጥ በ‹ጸጥታ ኃይሎች› ተከልክሏል፡፡

‹የአቸኳይ የሰላም ጥሪ› መግለጫውን ለመዘገብ አዲስ ማለዳን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙኀን መግለጫው ይሰጥበታል በተባለው ኢንተር ለግዠሪ ሆቴል የተገኙ ቢሆንም፣ መግለጫውን ሳይወስዱ እንዲመለሱ ተደርጓል። በቦታውም በርከት ያሉ ሲቪል የለበሱ ደኅንነቶች እንዲሁም የደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ አካላት ተገኝተው ነበር።

‹መግለጫው እንዳይሰጥ› የሚያደርገው ክልከላ በየትኛው የመንግሥት አካል የተሰጠ እንደሆነ ግን አልታወቀም፡፡

የመግለጫውን ጥሪ ያስተላለፈው የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ሲሆን፤ ‹የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አሳስቦን የተሰባሰብን ነን› ያሉ በርካታ አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም የተሳተፉበት ነበር።

Source: Link to the Post

Leave a Reply