በትግራይ ክልል የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በክልሉ የቴሌኮም አገልግሎት መቋረጡን እንዲሁም መጠነ ሰፊ የመረጃ መረብ ጥቃትና አገልግሎት የማስተጓጎል ሙከራዎችን ማምከኑን ኢትዮቴሌኮም አስታወቀ። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ከአንድ ወር በፊት ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ከ37 ደቂቃ ላይ በትግራይ ክልል አገልግሎት መቋረጡን አመልክተዋል።
Source: Link to the Post