#መጥፎ የአፍ ጠረን (bad breath)በአለም አቀፍ ደረጃ መጥፎ የአፍ ጠረን ከ4 ሰዎች 1ኛውን እንደሚያጠቃ ይገመታል።መጥፎ የአፍ ጠረን ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና ችግር ከሚያስከትሉ የተለ…

#መጥፎ የአፍ ጠረን (bad breath)

በአለም አቀፍ ደረጃ መጥፎ የአፍ ጠረን ከ4 ሰዎች 1ኛውን እንደሚያጠቃ ይገመታል።
መጥፎ የአፍ ጠረን ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና ችግር ከሚያስከትሉ የተለመደ ችግር መሆኑንም ይነገራል።

መጥፎ የአፍ ጠረን መንስኤዎቹን እንዲሁም ስለመፍትሄው እንዲነግሩን የጥርስ ሀኪም ከሆኑት ዶ/ር ቃልኪዳን ኤፍሬም ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡

#መጥፎ የአፍ ጠረን #ምንድነው?

መጥፎ የአፍ ጠረን(bad breath) ከተለያዩ ነገሮች መንስኤ ሊከሰጥ የሚችል የአፍ መጥፎ ሽታ መሆኑን ባለሙያዋ ያስረዳሉ፡፡
#መጥፎ የአፍጠረን በምን ሊታወቅ ይችላል?

– ማንኪያ ልሶ በማሽተት
– አፍ ይዞ ማሽተት
– ሌላ ሰው በማሸተት ማወቅ እንደሚቻል ባለሙያዋ ተናግረዋል

#መጥፎ የአፍ ጠረን መንስኤ
– የድድ መድማት
– የጥርስ በሽታ
– ወፍራም ምቅራቅ ያላቸው እና ምራቅ የማያመነጩ
– ሽታ ያላቸውን ምግቦች መመገብ
– የአፍ መድረቅ
– ምላስን አለማፅዳት ይጠቀሱበታል

#መጥፎ የአፍ ጠረንን መከላከያ መንገዶች
– በቀን ሁለቴ ጥርስን መቦረሽ
– በየሶስት ወሩ የጥርስ ማፅጃ ብሩሻችንን መቀየር
– ውሃ በደንብ መጠጣት
– በየ ስድስት ወሩ የህክምና ተቋም በመሄድ የጥረትሳችንን ጤንነት መከታተል
– ሁሌ ጥርሳችንን ስናፀዳ ምላሳችንን ማፅዳት
– ፍሎራይድ ያላቸውን የጥርስ ሳሙናዎች መጠቀም ይመከራል ብለዋል፡፡

እነዚህን ነገር በማድረግ የማይጠፋ ከሆነ ከውሰጥ ጤንነታችን ጋር ሊገናኝ ስለሚችል ከጥርስ ሀኪም ውጪ ያለ ዶ/ር ጋር በመሄድ መታየት እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የአፋችንን ጤንነት ለመጠበቅ እና መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳይመጣ በዋነኛነት የአፋችንን ንጽህና መጠበቅ እንደሚስፈልግ እና ጥርሳችንን
በምናፀዳበት ግዜም አፋችን ውስጥ የሚቀር ቁሻሻ እንዳይኖር ትክክከለኛውን መንገድ በመጠቀም ማጽዳት እንደሚስፈልግ ዶ/ር ቃልኪዳን ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply