መጪው ጊዜ የሰላም ይሆን ይሆን?! https://youtu.be/FTy6EvVLae4 (አሻራ ሹክሹክታ ጥር9፣ 2013 ዓ.ም) በኢትዮጵያ  ምድር የቡድን እና የዜግነት መብትን ለማጣጣም  ተብሎ ኢ…

መጪው ጊዜ የሰላም ይሆን ይሆን?! https://youtu.be/FTy6EvVLae4 (አሻራ ሹክሹክታ ጥር9፣ 2013 ዓ.ም) በኢትዮጵያ ምድር የቡድን እና የዜግነት መብትን ለማጣጣም ተብሎ ኢ…

መጪው ጊዜ የሰላም ይሆን ይሆን?! https://youtu.be/FTy6EvVLae4 (አሻራ ሹክሹክታ ጥር9፣ 2013 ዓ.ም) በኢትዮጵያ ምድር የቡድን እና የዜግነት መብትን ለማጣጣም ተብሎ ኢህአዴግ ወደ ብልፅግና ተቀይሯል፡፡ ኢህአዴግ የሉዓላዊ ድርጅቶች ግንባር ነበር፡፡ ብልፅግና ደግሞ ሉዓላዊ ግንባሮች ከስመው የፈጠሩት ውህድ ሀገራዊ ፓርቲ ነበር፡፡ በስሙ ውህድ እና ሀገራዊ ይባል እንጂ በይዘቱ የኢትዮጵያን የብተና መንገድ ያዘጋጀ ፓርቲ ነው ይለናል-በሹክታ የነገረን የመረጃ ምንጫችን፡፡ ለአብነት ሲያነሳ የአማራ ብልፅግና ከትግራይ፣ ከቢሻንጉል፣ ከኦሮሚያ ወዘተ እንዳይስማማ ሆኖ የተሰራ ነው፡፡ የፌዴራል መንግስቱ በዶክተር አብይ በኩል የትግራይ ብልፅግናን “የአማራ ብልፅግና መሬታችሁን እንዴት ትሰጣላችሁ? የእናንተ ነው !” ይላቸዋል፡፡ ይህንንም የትግራይ ጊዜአዊ አስተዳድር ዶክተር ሙሉ ነጋ ” አማራ ክልል ጋር ወዳጅነት አይኖረንም፡፡ ህግ ነው የሚዳኘን፡፡ ህዝባችን ችግር ላይ በወደቀበት ወቅት መሬት ወረራ ተደርጓል፡፡ የፌዴራል መንግስቱ ግን በአፋጣኝ እንደሚያስመልስልን ቃል ገብቶልናል” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ዶክተር ነጋ ይሄን ያሉት የኦሮሞ አባገዳዎች መቀሌ በነበሩበት ወቅት ነው፡፡ የአባገዳዎች ወደ መቀሌ መሄድም ፖለቲካዊ እንደነበር የሹክታ ምንጫችን ከቦታው ነግሮናል፡፡ ዶክተር ሙሉ ነጋ ከማንም የህወኃት አመራር በበለጠ አማራ ጠል እንዲሆኑ ብልፅግና አመቻችቶላቸዋል፡፡ ከአፋርም ሆነ ከኦሮሞ ጋር ወንድማማች ነን ፡፡ ከአማራ ጋር ይቅርብን የሚል ንግግር በይፋ ተሰምቷል፡፡ ሌላው የብልፅግና አደገኛነት የሰሜን ፖለቲካን ሙሉ በሙሉ ለማድከም መነሳቱ ነው፡፡ ትግራይ መቀሌን ጨምሮ በሻዕቢያ ወታደር ተወሯል፡፡ የዶክተር አብይ አማካሪ ሙሐመድ ዳህላን ነው፡፡ ዳህላን የተባበሩት የአረብ ኤሜሬት የግጭት ጠማቂ ደላላ ነው፡፡ ዳህላን ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋርም ይገናኛል፡፡ ለሳውዲም ወዳጅ ነው፡፡ የአረብ አብዮት አቀናባሪ ስለሆነ የአብዱል ፈታህ አልሲሲ የስልጣን ምንጭ ነው፡፡ ፍልስጤምን ለእስራኤል የሸጠ እንደሆነም ይነገርለታል፡፡ በሬሲብ ጠይብ ኤርዶጋን ላይ ከሁለት ዓመት በፊት መፈንቀለ መንግስት አድርጓል በሚል ተጠርጥሮ ነበር፡፡ ዳህላህን ግን ተሰወረ፡፡ ኤርዶጋን ዳህላንን የያዘ 10 ሚሊየን የቱርክ ገንዘብ እከፍላለሁ ብሎ ጫረታ እንዳወጣ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ዳህላን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የበለጠ በቤተመንግስት ይታያል፡፡ ከቤተመንግስት አልፎ ወደ ደቡብ ክልል ኮይሻ የመዝናኛ ቦታ ግንባታ ሂዷል፡፡ ዳህላን በህወኃት ላይ በተደረገው ዘመቻ በማገዝ እጁ አለበት የሚሉ ብዙ ናቸው፡፡ አረብ ኤሜሬት ምስራቅ አፍሪካን ለመያዝ በምታደርገው ጥረት ዳህላን ዋነኛ ሰው ነው፡፡ ከአሰብ እስከ ፑንትላንድ ወደቦች የአረብ ኤሜሬት ድርሻ ሰፍቷል፡፡ የሱዳን የአሁኑ መንግስትም ለአረብ ኤሜሬት ገባሪ ከመሆን አያልፍም፡፡ ይህ ሁሉ ጉዞ ለኢትዮጵያ የሚበጅ አይመስልም፡፡ ያም ሆኖ ግን መሃመድ ዳህላን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁነኛ ሰው እንደሆነ አሾክሿኪያችን መረጃ አድርሶናል፡፡ ዳህላን የካርቱም እና የአስመራን ፖለቲካ ይደግፋል፡፡ እንዲህ ከሆነ አስመራም ከትግራይ፣ ካርቱም ከአማራ ክልል አንወጣም ሊሉ ይችላሉ፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ሁለቱ ክልሎች እርስ በእርሳቸውም እንደገና ወደ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል የአማራ እና የትግራይ ህዝብ አይደለም ከኢትዮጵያ የመሃል ፖለቲካ ከምድረገፅ ሊጠፉ ይችላሉ፡፡ እንደ አሾክሿኪያችን ግዙፍ የልማት ድርጅቶች ሲሸጡ አረብ ኤሜሬት ከፍ ያለ ድርሻ ትገዛለች፡፡ ይሄን የሚቃወም ኢትዮጵዮጵያ ውስጥ ካለ እነ ዳህላን ቤተመንግስት ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን የብአዴን አመራሮች መረጃ የላቸውም፡፡ ቢኖራቸውም ነገ አይታያቸውም፡፡ በሌላ በኩል የቢሻንጉል ብልፅግና ሰው እንደ ቅጠል እያስጨፈጨፈ፣ አማራ እንዲወቀስ ብቻ ሳይሆን ጃዊ፣ ቻግኒ እና መተማ የቢሻንጉል ጉምዝ መሬት ነው እንዲሉ ብልፅግና አድርጓቸዋል፡፡ በአንፃሩ የራሳቸው መሬት በኦነግ እንዲያዝ ሆኗል፡፡ ጋሞ፣ ኮንሶ፣ጊዲዮ በኦነግ የመሰልቀጥ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ስለዚህ ዳህላን በኢትዮጵያ የዕርስ በዕርስ ግጭት ተነስቶ ኢትዮጵያ ለአረብ ኤሜሬት ገባሪ ሀገር እንድትሆን ሊያደርግ ይችላል፡፡ የየመን ፣ የሶሪያ እና የሉቢያ አለመረጋጋት ምንጩም እንዲህ አይነት የማይታረቁ ዓለምአቀፍ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለውጭ ሀይሎች ፍላጎት አሳልፋ የሰጠች ሲሆን፣ ህወኃት በምዕራባውያን ሰፊ ድጋፍ ነበረው፡፡ በህወኃት መውደቅ ምዕራባውያን አኩርፈዋል፡፡ በሌላ በኩል በህወኃት መውደቅ እነ አረብ ኤሜሬት ከመደሰት አልፈው ፣ ውድቀቱን አመቻችተዋል፡፡ የአማራ ብልፅግና ሚና ቢስ ስለሆነ ቀጣይ አውራው ፓርቲ የዶክተር አብይ አህመድ እንደሚሆን ግምት አለ፡፡ ይህም በአረብ ኤሜሬቶች በእጅጉ ይደገፋል፡፡ ይህ ሲሆን ኢትዮጵያ ዳግመኛ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት፣ ወደ ሰባዊ መብት ጥሰት፣ ወደ አምባገነነት እና ወደ መፈራረስ ልትሄድ ትችላለች፡፡https://youtu.be/FTy6EvVLae4

Source: Link to the Post

Leave a Reply