
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት የድንበር ግዛት መርሳቤት ሰላም ካጣ ሰነባብቷል። ችግሩ እየበረታ ሲመጣም የኬንያ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ ባልተለመደ መልኩ እርምጃ ለመውሰድ ተገድዷል። በመርሳቤት ለተፈጠረው የፀጥታ ችግር መንስኤ ድርቅ፣ ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እና በግጭት ከምትታመሰው ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ በቀላሉ መገኘቱ ነው ሲል የኬንያ መንግሥት ገልጿል።
Source: Link to the Post