#ሙዚቀኛ_ሐናን_አብዱ_የአሃለሎና_የአምባሰል_ወረዳ_የባህል_አምባሳደር_ሁና_ተሰየመች። ባህርዳር:- ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በሀይቅ ከተማ በተከበረው አ…

#ሙዚቀኛ_ሐናን_አብዱ_የአሃለሎና_የአምባሰል_ወረዳ_የባህል_አምባሳደር_ሁና_ተሰየመች። ባህርዳር:- ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በሀይቅ ከተማ በተከበረው አመታዊው የአሃለሎ ፌስቲቫል የተዳከመውን የወሎ የባህል ሙዚቃ በማነቃቃት የምትገኙው ሀናን አብዱ አምባሳደር እንድትሆን እና ለባህላዊ ሙዚቃ ላበረከተችው ስራ የ200 ሺ ብር ሸልማት ተበረከተላት። የወሎን ቱባ ባህል በማስተዋወቅ ፣የወሎየነትን መገለጫ የሆነውን “የአሆለሌ”የልጃረዶች ጨዋታ በሙዚቃ አቀናብራ በማዘጋጀቷ ና ለህዝብ ተደራሽ በማድረጓ የባህል አምባሳደርነት ካባ ተላብሳለች። አርቲስት ሀናን አብዱ ተወልዳ ያደገችው በደቡብ ወሎ ዞን አምባሠል ወረዳ ውጫሌ ከተማ ሲሆን በስርቅርቅ ድምጿ በባህል ሙዚቃው ዘርፍ አድናቆትን አትርፋለች።አርቲስቷ አርከባስ፣አግራው፣ሆላሌና ሌሎች ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎቿን ለአድናቂዎቿ አበርክታለች።ሙዚቃዎቿ የሚያጠነጥኑት በተወዳጅ ቱባ ባህሎቻችን ዙሪያ በመሆኑ ለወሎ ህዝብ የባህል እሴት ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ከስራዎቿ መካከል በበርካታው ማህበረሰብ ዘንድ ተደማጭነቱ የሚታወቀው “አሆላሌ” በምስራቁ የደቡብ ወሎ ክፍል በልጃገረዶች ተዋናይነት የሚከወን አማላይና ኪነጥበብ አዘል ባህላዊ ሁነት በመሆኑ የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ትኩረት ሰጥቶት ይሄ አማላይ ባህል እውቅና እንድያገኝ ታስቦ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሁለደሬ መዲና በሆነችው ሀይቅ የባህል ፌስቲቫል እንዲከበር አድርጓል። ባህሉ ከስር መሠረቱ ያለውን ትርጓሜና ፋይዳ በተመለከተ ምሁራን ጥናት አድርገውበት ቀርቦ ይሁኝታን አግኝቷል። ይሄን ማራኪና ህዝባዊ መሠረት ያለው ባህል ለዚህ እንዲበቃ በሙዚቃ ክሊፕ በማውጣት የበለጠ ጎልቶ እንዲወጣ ያደረገችው አርቲስት ሀናን አብዱ በመሆኗ የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ከኪነጥበብ ቤተሠቦቹ ጋር በመሆን የአሆላሌ ውብ ባህል አምባሳደር አድርጎ ሾሟታል ሲል የለገሂዳ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል። የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅትም ለአርቲስት ሀናን አብዱ ላበረከተችው አስተዋጽኦ እያመሰገነ እነዚህ እንኳንስ ደስ የመለሽ ማለት ይፈልጋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply