
ወጣቱ ድምጻዊ ጀምበሩ ደመቀ፣ ከዛሬ 50 ዓመት በፊት የጃዝ ሙዚቃ ንጉሥ ሙላቱ አስታጥቄ የሰራውን አይፈራም ጋሜ የተሰኘ ሙዚቃ ለዚህ ዘመን የሂፕ ሆፕ አድናቂ አንዲሆን አድርጎ ሰርቶታል።ጋሽ ሙላቱ አስታጥቄም በሙዚቃ ቪዲዮው ላይ አብሮ ተሳትፏል።ጀምበሩ በስሙ በሰየመው አልበሙ የተለያዩ ሙዚቀኞች ስራን ሳምፕል ያደረገ ሲሆን የዘመኔ ድምጽ ነው ያላቸውን የተለያዩ ስራዎች አቅርቧል።ቢቢሲ በስራዎቹ ዙሪያ ከጀምበሩ ጋር ቆይታ አድርጓል።
Source: Link to the Post