ሚስጥራዊና አገር አፍራሽ ስብሰባ አድርጓል ተብሎ ፈቃዱ የተሰረዘው የሰላምና ልማት ማዕከል ወደ ሥራ መመለሱ ተገለጸ፡፡ ባህርዳር:- መጋቢት 21/2014 ዓ.ም…

ሚስጥራዊና አገር አፍራሽ ስብሰባ አድርጓል ተብሎ ፈቃዱ የተሰረዘው የሰላምና ልማት ማዕከል ወደ ሥራ መመለሱ ተገለጸ፡፡ ባህርዳር:- መጋቢት 21/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተገናኘ በኅዳር ወር ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተላለፍ የድርጅቱ የቦርድ አባላት፣ ‹‹በድብቅ አገርን ለማፍረስ›› ተንቀሳቅሰዋል በሚል ፈቃዱ ተሰርዞባቸዉ እንደነበር ይታወሳል ፡፡ በእነ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ የሚመራው ‹‹የሰላምና ልማት ማዕከል›› የተሰኘ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት፣በአሁኑ ሰአት ፈቃዱ ታድሶ ከአንድ ወር በፊት ወደ ሥራ መመለሱ ተገልጿል፡፡ የድርጅቱ ኃላፊዎች አገር አፍራሽ የሆነ ሚስጥራዊ ስብሰባ ማካሄዳቸዉ ለፍቃዱ መታገድ ምክንየት ነዉ ያሉት የሲቪል ማኅበረሰቦች ባለሥልጣን የሕግ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ምሥጋናው በሚስጥራዊ ስብሰባው ተሳትፈዋል የተባሉት የድርጅቱ የቦርድ አባላትን እንዲታገዱ በማድረግና አዳዲስ የቦርድ አባላት በመምረጥ ድርጅቱ ወደ ሥራው እንዲመለስ መወሰኑን ከሪፖርተር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply