ሚኒስቴሩ የ12ኛ ክፍል ፈተና  በስኬት  እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ  ጥሪ አቀረበ

ሚኒስቴሩ የ12ኛ ክፍል ፈተና  በስኬት  እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ  ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና  በስኬት  እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ  ጥሪ አቅርቧል።

ሚኒስቴሩ የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ስርጭትን አስመልክቶ ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር    ጌታሁን መኩሪያ ÷ፈተናው በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንዲከናወን ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ  ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሩ ሀገር አቀፍ ፈተናውን በተያዘለት የግዜ ገደብ ለመስጠት እና ለማጠናቀቅ  አስፈላጊው ዝግጅት ማድረጉንም  አስታውቀዋል።

የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር  ዶክተር ዲላሞ ኦተሬ በበኩላቸው÷ ፈተናው በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ በከፍተኛ ጥንቃቄና ቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከየካቲት 21  እስከ  26 ቀን 2013 ድረስ የመፈተኛ ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ሥራ እንደሚጠናቀቅም በውይይቱ ተገልጿል።

በመሆኑም ፈተናው በሚፈለገው አግባብ እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት፣የትምህርት ማህበረሰቡና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት የጀመሩትን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ  ሚኒስትሩ  ጥሪ  አቅርበዋል፡፡

የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ከየካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ መገለፁ ን ከሚኒስቴሩ ገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

The post ሚኒስቴሩ የ12ኛ ክፍል ፈተና  በስኬት  እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ  ጥሪ አቀረበ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply