ሚና ቢስ ባለወንበሮች  (አሻራ ጥር 5፣ 2013 ዓ.ም) ከብአዴንነቱ ብዙ ያልተላቀቀው የአማራ ብልፅግና በመተከል ጉዳይ ጣቱን በአፉ ጭኖ አሸናፊ ለመሰለው ሁሉ አራግቢ ሆኗል የሚሉ አስተያይቶ…

ሚና ቢስ ባለወንበሮች (አሻራ ጥር 5፣ 2013 ዓ.ም) ከብአዴንነቱ ብዙ ያልተላቀቀው የአማራ ብልፅግና በመተከል ጉዳይ ጣቱን በአፉ ጭኖ አሸናፊ ለመሰለው ሁሉ አራግቢ ሆኗል የሚሉ አስተያይቶ…

ሚና ቢስ ባለወንበሮች (አሻራ ጥር 5፣ 2013 ዓ.ም) ከብአዴንነቱ ብዙ ያልተላቀቀው የአማራ ብልፅግና በመተከል ጉዳይ ጣቱን በአፉ ጭኖ አሸናፊ ለመሰለው ሁሉ አራግቢ ሆኗል የሚሉ አስተያይቶች እየጎረፉ ነው፡፡… የሚናገሩት ከጭንቅላታቸው ሳይሆን ከጉንጫቸው ነው የሚባልላቸው የአማራ ብልፅግና አመራሮች አንዳቸውም በግል የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ሆነ በሚዲያ መግለጫ አልሰጡም፡፡ ከዚህ በፊት የተንፈራገጡት ሁሉ ፀጥ ብለዋል፡፡ እንመራዋለን የሚሉት ህዝብ ከአሟሟቱ እስከ አቀባበሩ ዘግናኝ ሲሆን ፣ የሚናገሩትም ሆነ የሚተገብሩት ነገር ጠፍቶባቸዋል፡፡ በዓላማቢስነት፣በወኔ አልባነት እና በፖለቲካ ድንቁርና ክፉኛ የሚታሙት ብአዴናዊያን ለአማራ ህዝብ የአንድን ግለሰብ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ያህል እንኳ ሚና አጥተዋል፡፡ ፀጥ በሉ ሲባሉ ፀጥ ይላሉ፡፡ የሀገሪቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት፣ ደህንነት፣ ንግድ፣የውጭ ፣የገቢዎች የመሳሰሉትን ሚኒስትር መስሪያቤቶች እየመሩ ህዝባቸው በዓለም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲጨፈጨፍ የጨፍጫፊው አጫፋሪ ሆነው መቆማቸው ከብአዴንነት የባሰ አመል እንደሆነ በፖለቲካ ቋንቋ እየተነገራቸው ነው፡፡ የሀገሪቱ ብልጽግና ፅህፈትቤት ሀላፊም ብአዴን ነበር፡፡ ነገር ግን ብአዴናዊያውን ከመታዘዝ ያለፈ ዓላማ ስለሌላቸው ሀገሪቱ በላያቸው ላይ እየፈራረሰች አማራ ሲጠቃ ደፍሮ የመናገር ወኔ እንኳን የሌላቸው ከሰውነት ክብር ያነሱ ካድሬዎች ሆነዋል፡፡ የብልጽግና ፖለቲካ ከኢህአዴግ በባሰ የአማራ ጠላትነቱን በግድያ አሳይቷል፡፡ የአማራ ወኪሎችም አድርባይነታቸው ከብአዴንነታቸው በላይ ሆኗል፡፡ በንፁሃን ሞት ላይ ወንበራቸው ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ሚና ቢስ ባለወንበሮች እስካሉ ድረስ የአማራ መጠላት፣ መፈናቀል እና ሞት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህል ይሆናል፡፡ ሚና ቢስ ባለወንበሮች ከከርሳቸው የዘለለ የሚኖሩለት ዓላማ ስለሌላቸው 27 ዓመትን ለህወኃት ህዝባቸውን አስገብረው፣ ሌላኛውን ቀጣይ ደግሞ ለተረኛው ሀይል ለማሻሻጥ ከወንበራቸው ላይ አንቀላፍተዋል፡፡ ፖለቲካ ቁማር ነው፡፡ ቁማሩንም በልተነዋል፡፡ አሳምነንም አወዛግበንም በብልፅግና ሰበብ እንመራችኃለን ተብለው እየተመሩ መሪ ለመሆን ወንበራቸውን ለሆዳቸው ነክሰዋል፡፡ ተከላካይ ደጋፊዎቻቸው ደግሞ፣ ብአዴን በክልሉ እንጂ በሰው ክልል አያገባውም እያሉ ያጃጅላሉ፡፡ ህወኃት መተከል ላይ ገደለ እያሉ ብአዴን ማዳን አይችልም ይላሉ፡፡ ወንበራቸው ለሆዳቸው ካልሆነ ንፁሃንን ያድን ነበር፡፡ ባያድን እንኳን ይቆረቆር ነበር፡፡ ግን የሚቆረቆሩትም ከተራ ስብከት የዘለለ አይደለም፡፡ አሁን ደግሞ በቁማር አሸናፊዎች ትዕዛዝ ተራ ቧልታቸውን እንኳን እንዳይናገሩ ሆነዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply