“ሚዲያን በማዘጋት የሚቆም ትግል የለም!” ሲሉ የራስ ሚዲያ አዘጋጆች ገለጹ፤ ኦህዴድ መራሹ ስርዓት በተደጋጋሚ ሲያግደው ከቆዬ በኋላ አሁን ላይ እስከመጨረሻው ሚዲያውን ያዘጋ ስለመሆኑ ጠቁመዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በእምየ ምኒልክ ዓርማ እና “ራስ ሚዲያ”(RasMedia) በተሰኘ መጠሪያ ለድምፅ አልባው ሁሉ ድምፅ በመሆን ላለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ስንሰራበት የነበረውን ሚዲያ ኦህዴድ/ኦነግ ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል በትናንተናው ዕለት አዘግቶብናል። በዚህ ሚዲያ ውስጥ:_ አንጋፋው የታሪክ ሙሁር እና ጋዜጠኛ ታዲዎስ ታንቱ (በዕስር ላይ የሚገኙ)፣ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው (ከመኖሪያው የተፈናቀለ)፣ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው (ከመኖሪያው የተፈናቀለ)፣ጋዜጠኛ ሙልዬ ንጋት (የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅ)፣ የመሳሰሉ ጠንካራ፣ታማኝ እና ፅኑ ባልደረቦች ይዞ ይገኛል። ከሁለት ዓመት ተኩል በላይ በፅናት ተጉዟል፤ ይሁን እንጅ የኦህዴድ/ኦነግ ስርዓት ለተለያዩ አካላት ዳጎስ ያለ ገንዘብ በመክፈል ከ60ሺህ በላይ ሰብስክራይበር የነበረውን #RasMedia ከሶስት ጊዜ በላይ ለአጭር እና ለረጅም ጊዜ ሲያሳግደው ከቆየ በኋላ ጥር 19/2015 ከነጭራሹ አዘግቶታል። ምንም አይነት ክፍያ እንዳይሰጥም ሆኖ ቆይቷል። በሚዲያችን እና በጋዜጠኞቻችን በኦህዴድ/ኦነግ ስርዓት በተደጋጋሚ የሚደርሰውን አፈና ተቋቁመን፣ሌላ #RASMEDIA INTERNATIONAL” የተሰኘ ሚዲያ ከፍተን የነበረ ቢሆንም ሰርዓቱ በትናንትናው ዕለት አዲሱን ሚዲያ ጭምር አዘግቶብናል። በመሆኑም ዛሬም ለህዝባችን ድምፅ ለመሆን ስንል ለሶስተኛ ጊዜ አዲስ “Ras Media Network (ራስ ሚዲያ መረብ) የተሰኘ ከፍተናል። በመሆኑም ወቅታዊ፣ፈጣን እና ሃቀኛ መረጃ ከምንጩ ማግኘት የምትፈልጉ በውጭና በሃገር ውስጥ ያላችሁ እና የትግሉ አንድ አካል የሆናችሁ በሙሉ ከታች የተያያዘውን አዲሱን ሚዲያ ሰብስክራይብ፣ላይክ እና ሼር በማድረግ እንድትቀላቀሉ በታላቅ አክብሮት አንጠይቃለን!! ሚዲያን በመዝጋት የሚቆም ትግል የለም!! አዲሱ የRas Media Network ሊንክ👉https://www.youtube.com/channel/UCujC4n1NwGCee_z-PCGSDyQ… እናመሰግናለን!!!
Source: Link to the Post