ማሊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሃይሎች በሀገሪቱ የሚደርሱ ጥቃቶችን እንዲመረምሩ የቀረበውን ጥሪ ውድቅ አደረገች።ማሊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታዉ ምክርቤት ያዘ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/sc7H5FFLGsYBtby1a8U4RrBAng2JelQ3mi7vgmb0diZcbUwXIX19dnepTBzXZu4IEoaAwHvS9hnQb3va-Gy-zI3wjuletoOkqsTtcmexgtJqYQdOdcfPmmG0720gWEWFCIRfZiFrZGW0FgV9T3lBXVlMGupgo8mJE_Sc2LAE6xYRCTPujLd5I2NndJhxPTkRBWE6X74P8NINpyXINT_tE-gWMkeK982mCKAEBSBczjoS8EWHix0BUJdRXfy747r8F3g8JBwFhY_KwY6vUs5N5jJUlrB-sJFc1-OpEHIELDU9ayruuvBUjw5_Iu7FfMd2B-Xlzd5JeR34TAz9mS6lpA.jpg

ማሊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሃይሎች በሀገሪቱ የሚደርሱ ጥቃቶችን እንዲመረምሩ የቀረበውን ጥሪ ውድቅ አደረገች።

ማሊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታዉ ምክርቤት ያዘዘዉን የሰላም አስከባሪ ሃይሎች በሀገሯ ተንቀሳቅሰዉ የሚደርሱ ሰብዓዊ ጥሰቶችን ይመርምሩ የሚለውን ትዕዛዝ በፍጹም እንደማትፈቅድ አስታዉቃለች፡፡

የማሊ ወታደራዊ መንግስት በ 2020 ስልጣን ሲይዝ ከቀድሞ ቅኝ ገዢዉ ፈረንሳይ ጋር የነበረዉን ግንኙነት ያቋረጠ ሲሆን፣ ከ10 ዓመታት በላይ ሀገሪቷን እየፈተነ የሚገኘዉን የታጠቀ ቡድን በጋራ ለመዋጋት የሩሲያ ዋግነር ግሩፕ የተሰኘ የግል የዉትድርና ኮንትራክተር ቦታዉን ተክቷል፡፡

እንደ ተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ቡድን ገለጻ ፤ ከጥር እስከ መጋቢት ድረስ 320 በማሊ ወታደሮች የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን አጣርቻለዉ ብሏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የማሊ ተወካይ ኢሳ ኮንፎሩ ፣ ‹‹ምንም እንኳን ትዕዛዙ ከተባበሩት መንግስታት የጸጥታዉ ምክርቤት ቢመጣም የማሊ መንግስት ፍቃድ በሌለበት ማንኛዉም ዓይነት እንቅስቃሴ ሊደረግ አይችልም ››ብለዋል፡፡ ተፈጥረዋል ለተባሉ የመብት ጥሰቶች ምርመራ የማድረግ ሃላፊነት ያለባት ማሊ ብቻ ናት ሲሉም አክለዋል፡፡

ምርመራ ከሚደረግባቸዉ ጉዳዮች በሞዉራ ከተማ የተከሰተዉ የማሊ ወታደሮች በነጭ ተዋጊዎች ጭምር በመታገዝ አድርገዉታል የሚባለዉ አሸባሪ ናቸዉ ተብለዉ የተጠረጠሩ ከ 100 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን ዜጎች የተገደሉበት ጉዳይ አንዱ ነዉ፡፡

የጸጥታዉ ምክርቤት ለ9 ዓመታት በሀገሪቱ የነበረዉን ሚንሱማ የተሰኘ የሰላም አስከባሪ ሃይል ቆይታ ለ12 ወራት ያረዘመ ሲሆን፣ 13 የድጋፍ ድምጽ ሲያገኝ ቻይና እና ሩሲያ ድምጸ ተዓቅቦ ማድረጋቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply