ማላዊያን በሐገራቸው የሚገኙ የፈረንሳይ ወታደሮች ለቀው እንዲወጡ ጠየቁ፡፡

በምዕራብ አፍሪካ በምትገኘው ማሊ በርካታ የታጠቁ ሽብርተኞች መኖራቸውን ተከትሎ ነው ፈረንሳይ በሺ የሚቆጠሩ ወታደሮቿን በሐገሪቱ ያሰማራችው፡፡ይሁን እንጂ ሐገሪቱ ከተደጋጋሚ ጥቃት አላመለጠችም፡፡ በሐገራቸው የሚገኙ ሽብርተኞች የጦር መሳሪያቸውን ባይፈቱም የፈረንሳይ ወታደሮች ግን ማሊን ለቀው እንዲወጡ የሐገሬው ዜጎች ጠይቀዋል፡፡የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በበኩላቸው በቀጠናው የሚገኙ ወታደሮቻቸውን ጉዳይ እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸው፣ በቅርቡ የወታደሮች ማስተካከያ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ጎልማሳው ፕሬዚዳንት ማሻሻያ ይደረጋል ይበሉ እንጂ ማሻሻያው እንዴትና መቼ  እንደሚደረግ በግልጽ አልተናገሩም፡፡የፕሬዚዳንቱን መልስ ተከትሎ በማሊ የሚገኙ የፈረንሳይ ወታደሮች መውጫቸው ደረሰ የሚሉ ዘገባዎች በስፋት እየተሰራጩ ነው፡፡ በማሊ የታጠቁ ኃይሎች በተለያየ ጊዜ ባደረሷቸው ጥቃቶች የፈረንሳይ ወታደሮችን ጨምሮ በርካታ ዜጎች መገደላቸው በማስታወስ ዘገባውን ያሰፈረው ቢቢሲ ነው፡፡

***********************************************************************

ቀን 19/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post ማላዊያን በሐገራቸው የሚገኙ የፈረንሳይ ወታደሮች ለቀው እንዲወጡ ጠየቁ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply