ማላዊ በኢየሩሳሌም ኤምባሲዋን ልትከፍት መሆኑን ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2013 ማላዊ በኢየሩሳሌም ኤምባሲዋን ልትከፍት መሆኑን ይፋ አደረገች::በእስራኤል የስራ ጉብኝት ያደረጉት የማላዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይዘን አወር ምካካ ውሳኔውን ግልፅና ጠቃሚ ብለውታል፡፡የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋቢ አሽኬናዚ በበኩላቸው የማላዊን ኤምባሲ በቅርቡ በእየሩሳሌም ከተማ ሲከፈት ማየት ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የሷን ፈለግ እንደሚኬተሉ ተስፋ አለኝ ብለዋል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘደበው አይዘን አወር ምካካ በጉብኝታቸው ወቅት እስራኤል ከአረቡ ዓለም ያደረገችውን የዲፒሎማሲ ስምምነት በማንሳት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ስኬት በመሆኑ ለሀገሪቱ መሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈውላቸዋል፡፡ማላዊ ኤምባሲዋን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2021 የመክፈት ሀሳብ እንዳላት ከቴል አቪቭ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

የማላዊ ፕሬዚዳንት የቅርብ ረዳት የሆኑት ብሪያን ባንዳ ስለሁኔታው ተጠይቀው በሰጡት መልስ ሀገራቸው ኤምባሲዋን በቀጣዩ ዓመት ኢየሩሳሌም ላይ ለመክፈት ዝግጅቷን ስለማጠናቀቋ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡በርካታ ሀገራት የተቃወሙትን የእየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማነት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እውቅና መስጠታቸውን ተከትሎ ጥቂት ሀገራት ኤምባሲያቸውን ወደ እየሩሳሌም ለማዛወር ሀሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply