You are currently viewing ማሩኝ›› የምትልበት ከመምጣቱ በፊት ‹‹በቃኝ›› በል! ~~~~~~~~አሳዬ ደርቤ~~~~~ ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 18/2014 ዓ.ም…                    አሻራ ሚዲያ ይህቺን ሕጻን አ…

ማሩኝ›› የምትልበት ከመምጣቱ በፊት ‹‹በቃኝ›› በል! ~~~~~~~~አሳዬ ደርቤ~~~~~ ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 18/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ይህቺን ሕጻን አ…

ማሩኝ›› የምትልበት ከመምጣቱ በፊት ‹‹በቃኝ›› በል! ~~~~~~~~አሳዬ ደርቤ~~~~~ ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 18/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ይህቺን ሕጻን አስታወሳችኋት? ከመንፈቅ በፊት ከምዕራብ ወለጋ ጭፍጨፋ አምልጠው ከተፈናቀሉ አማራዎች ጋር ያገኟት ጋዜጠኞች ሲጠይቋት የሰጠችው መልስ እንደሚከተለው ነበረ፡፡ ‹‹ስምሽ ማን ነው?›› ‹‹አንሻ ሠኢድ›› ‹‹የት ነበር የምትኖሪው?›› ‹‹ዳንዴ ቀበሌ›› (ምዕራብ ወለጋ) ‹‹በምን ምክንያት ነው ያፈናቀሏችሁ? ‹‹ነፍጠኛ ናችሁ ነው የሚሉት›› ‹‹ነፍጠኛ ማለት ምን ማለት ነው?›› ‹‹ወላሂ አላውቀውም!›› በጣም የሚያሳዝነው ነገር ታዲያ ያን ጊዜ ይህቺ ሕጻን በየዋህ አንደበቷ ብሶቷን ስታወራን ባለመቆጣታችን እና ጥቃቷን ባለማስቆማችን የተነሳ በቅርቡ ደግሞ የአንሻን የመፈናቀል እድል የተነፈጋት ሕጻን ‹‹ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም›› የሚል ልመናዋ ዋጋ አጥቶ ከሺህ ከሚቆጠሩ አማራዎች ጋር ተገደለች፡፡ እይውልህ ወንድማለም…. ያለ መንግሥት ፍላጎት የሚፈጸምን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማስቆም የመጀመሪያ እርምጃ የተፈጸመውን ወንጀል ዜጎች እንዲያወግዙትና እንዲማሩበት ማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛው እርምጃ ደግሞ ወንጀለኛውን መቅጣት ወይም ደግሞ ማጥፋት ነው፡፡ በአማራዎች ላይ የሚፈጸመው ጭፍጨፋ ግን በመንግሥት የሚቀነባበርና አገር አፍርሶ አዲስ አገር የመሥራት ግብ ያለው በመሆኑ በመቶዎችና በሺህዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን በተገደሉበት እለት መንግሥት አትክልት ውስጥ ሲደበቅ ታየዋለህ፡፡ አንተ ‹‹ይሄን ያህል ሕይወት ከገበርን አይበቃም ወይ?›› እያልክ ስትጮህ እሱ ‹‹መቼ ተጀምሮ ነው የሚያበቃው›› የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው በሚችል ዝምታ ያልተቀበረ አስከሬን ተራምዶ ችግኝ ሲተክል ትመለከተዋለህ፡፡ በክልሉ ውስጥ የፈጸመብህን ጥቃት የሚያስረሳ፣ ያንተን ሥም በክፉ የሚያስነሳና ለሌላ ዙር ጭፍጨፋ የሚያነሳሳ… በቪዲዮ የተደገፈ ጥቃት በክልልህ ውስጥ አቀናብሮ የወንጀሉ ተጋሪ ካደረገህ በኋላ እንባህን ቀምቶ ደምህን ሲያፈስስ ታገኘዋለህ፡፡ እናም እልኻለሁ… የተፈጸመብን ጉድ ወደፊት ከታቀደልን እቅድ ጋር ሲነጻጸር ኢምንት ነው፡፡ ያለፈው አረመኔያዊ ድርጊት ወደፊት ከሚከሰተው ጥፋት ጋር ሲወዳደር ምንም ነው፡፡ ‹‹አትንካኝ›› ብለህ መነሳት እስካልቻልክ ድረስ ከትንሽ ጊዜ በኋላ የአማራ ሕዝብን ቀርቶ ብአዴንን በሚያስደነግጥና ለመላው ዓለም በሚሰቀጥጥ አረመኔያዊ ማንነት ሲመጣ ታየዋለህ፡፡ ኦነግን ያጠፋዋል ብለህ ስትጠብቅ ብልጽግናን አክስሞ ቶሌ ቀበሌ ላይ ያየኸውን ዘግናኝ እልቂት ቦሌ ድረስ ሲያመጣው ትታዘባለህ፡፡ አሁን ላይ እንደ ሕዝብ ‹‹ወገኔን አትግደሉ›› ብሎ መቆጣት የሚያመጣውን እስራት ፈርተህ ስትርመጠመጥ፣ የሆነ ጊዜ ላይ በቤተሰብና በግለሰብ ደረጃ ከአፈሙዝ ስር ተንበርክከህ ‹‹እባካችሁ እኔን አትግደሉኝ›› እያልክ ስትማጸን እራስህን ታገኘዋለህ፡፡ እናም ይህ እንዳይሆንብን የምንሻ ከሆነ፣ እጅና እግራችንን አስረው ከገጀራ ስር ሊጥሉን የሚሞክሩ የክልል አመራሮችን እና ፖለቲከኞችን ‹‹ይሄን ማድረግ አትችሉም›› እንበላቸው፡፡ እራሳችንን አንቅተን ሕዝባችንን እንቀስቅሰው፡፡ ሥልጣን ላይ ያለው ኃይል ከፋፍሎ ሊውጠን ሲያስብ አንድ ሆነን እንትፋው፡፡ እስካሁን ለጥፋት የዳረገን አስተሳሰብ ‹‹ወገኔን አትንኩብኝ›› በሚል ሕዝባዊ ቁጣ አስፈሪ ሆነን በመገኘት ፈንታ ‹‹እኔን ምን አገባኝ›› በሚል የፍርሐት አሮንቃ ውስጥ መዘፈቃችን ነውና በጅምላ የታወጀብንን እልቂት በጋራ እናክሽፈው፡፡ share ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply