ማርች 8 በማስመልከት ዕንቁ የተባለ ልዩ የብድር አገልግሎት ማስጀመሩን አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና የብድር ህብረት ስራ ማህበር አስታወቀ።እስከ 12ሚሊዮን ብር ለሴቶች ብድር ለመስጠት ማሰቡንም…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/RPq37NzB4UOCKQ51sGDInLqVlz4hAxY2LwDJK2EXWgmgVY5w65bO8RpPdEt1y2D8b18X3ExVkGRHoSNMSIhu3tlzcsanR-epNtoVPg2SdTgcGLRvVV0BnH0tr_W9Ze_zhJ2BROHmGUGKeNv2PgkrKgWx8dfmWkbPAjlbwmkCCMDuIhoIDWeEmO4m5IbbjPCHNHGTho-PH34ORAPJX0psurg6NsplPtqcVLq-x9q9IKpjxW7LzESstRbpgjeCX5aqh3OivnkVXJxv2laXaEUMRPd9ojlJ73_QSgnWJ3s0EcFDcsXDI-C0qnerNkYXyzxBFw8RM9kidUzPw2dL1Yn01Q.jpg

ማርች 8 በማስመልከት ዕንቁ የተባለ ልዩ የብድር አገልግሎት ማስጀመሩን አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና የብድር ህብረት ስራ ማህበር አስታወቀ።

እስከ 12ሚሊዮን ብር ለሴቶች ብድር ለመስጠት ማሰቡንም የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ፍፁም አብርሃ ተናግረዋል።

ማህበሩ ይህ ልዩ የሴቶች የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ለሁለት ሳምንት እንደሚቆይ አመልክቷል።

በዛሬዉ ዕለት የሴቶችን ቀን በማሰብ በተዘጋጀዉ መርሃ ግብር ላይ አስተያየታቸውን ለሚዲያዎች የሰጡት አቶ ፍፁም ማህበሩ በ11 ዓመታት ዉስጥ 2ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

አሚጎስ ካለዉ 100 ሰራተኛ 53 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸዉ የተነሳ ሲሆን ከ50 በመቶ በላይ ሴት ሰራተኞች መኖሩ ተገልፃል።

በመሆኑም ለሴቶች ልዩ የብድር እና ቁጠባዉ ከተለመደዉ በተቀማጭም በወለድም ቅናሽ ማዘጋጀቱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ዕንቁ ከሌሎች ብድርና ቁጠባዎች የ1በመቶ ቅናሽ ያለዉ ሲሆን የመክፈያ ግዜዉም ከተለመደዉ ረዘም ያለ መሆኑ ተገልፃል።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና የብድር ህብረት ስራ ማህበር በዛሬዉ ዕለት 113ኛዉን የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ከሴት የተቋሙ ሰራተኞች እና ከሴት ተበዳሪ አባላቱ ጋር በጋራ አክብሯል።

በአቤል ደጀኔ

የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply