ማስተንፈሻ መሰል እርምጃ በመውሰድ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ግድያና በደል ማስቀም ስለማይችል መንግስት የማያዳግም እርምጃ ነው መውሰድ ያለበት ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ገለጹ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በህጹሀን ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃቶች እየተሰነዘሩ ነው፡፡ከቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በስፋራው ሂደው ከነዋሪዎችና አመራሩ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፤ ይሁንና በውይይቱ ማግስት በዜጎች ላይ የሚደርሰው ግድያ መቆም አለመቻሉ ብዙዎችን አስቆጥቷል፡፡

ጠበቃና የህግ አማካሪ አቶ ነብዩ ምክሩ እደሚሉት፤ መንግስት የህግ የበላይነትን ያስከብር የሚለው ቃል ፖለቲካዊ ንግግር ነው፤ የማስከበር ተግባር ውይይትና ድርድር ውስጥ የሚገባ አይደለም ይላሉ፡፡

መንግስት በህውሓት ላይ የህግ ማስከበር ስራን በጥቂት ሳምንታት አከናውኖ በመተከል ላይ የሚደርሰውን ግድያና በደል ለማስቆም ሶስት አመት ማስታመሙ ተገቢነት የሌለው ተግባር ነው ሲሉ የህግ ባለሙያው የመንግስትን አካሄድ ወቅሰዋል፡፡

 አዘጋጅ: ጸጋነሽ ደረጀ

Source: Link to the Post

Leave a Reply