ማስኮን ካላደረጉ አገልግሎት አያገኙም የተሰኘው ንቅናቄ በሚቀጥሉት ሳምታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን የጤና ሚኒስቴሩ ገለፀ።

በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በየጊዜው እየጨመረ ቢመጣም በህብረተሰቡ ዘንድ እየታየ ያለዉ መዘናጋት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገልጿል።በህብረተሰቡ የታየው መዘናጋት ዋጋ እንዳያከፍል ማስክ ያላደረገ በተቋማት በኩል አገልግሎት እንዳያገኝ “ኖ ማስክ ኖ ሰርቪስ ” የተሰኘ ንቅናቄ በሀገር ደረጃ እንደሚጀመር ተገጾ ነበር።

አሀዱም ንቅናቄውን የማስጀመር ተግባር ከምን ደረሰ ሲል ሚኒስቴሩን ጠይቋል። የጤና  ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ጀረጄ ዱጉማ ለአሀዱ እንደገለጹት ንቅናቄው በክልል ደረጃ ተግባራዊ መሆን የጀመረ ሲሆን መዲናዋን ጨምሮ በሌሎች አከባቢዎች በሚቀጥሉት ሳምታት ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል።

የግልና የመንግስት ተቋማት መመሪያውን ተፈጻሚ እንዲያደርጉ በቂ ግንዛቤ መሰጠቱን ዶ/ር ደረጄ ገልጸው በንቅናቄው ዘመቻ የህግ አካላት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል። በሀገሪቱ የማስክ እጥረት የሌለ ቢሆንም የተጠቃሚው ቁጥር ከቀድሞ ማሽቆልቆሉን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።የማስክ አጠቃቀምን ጨምሮ መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ ከጠቅላይ አቃቤ ህግና ከፍትህ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

*****************************************************************************************

ቀን 30/04/2013

አሀዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply