ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ የተመሠረተበትን 20ኛ አመት እያከበረ ነው።

በ 4 ዓመት ዕድሜው በደም ካንሰር ህይወቱ ባለፈ ልጃቸው ስም የተመሠረተው የካንሰር ማዕከል 20 አመት እንደሞላው ከመስራቾቹ አንዱ የሆኑት አባቱ አቶ ወንዱ በቀለ ገልፀዋል።

በመኖሪያ ቤታቸው የተመሠረተው ማዕከሉ አሁን ላይ ከ1ሺህ 5መቶ በላይ አባሎችን ይዟል።

5መቶ የበጎ ፈቃድ ሰራተኞች መኖራቸውን የገለፁት የማህበሩ መስራች አቶ ወንዱ በቀለ ፤ 30 ቋሚ ሠራተኞችን ይዞ 8 ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ማዕከሉ ከካንሰር ህመም በተጨማሪ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ላይም በመስራት ላይ እንደሚገኝም ነው የገለፁት።

ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ በሰራቸው የተለያዩ ስራዎች በ6 ዓመት ውስጥ 5 ዓለምአቀፍ እና 2 አገር አቀፍ ሽልማቶችን ማግኘቱም ተገልጿል።

ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ ትኩረቱን በህፃናት ካንሰር ላይ አድርጎ የሚሰራ ማዕከል ነው።
ማዕከሉ በ15 መስራች አባላት ከዛሬ 20 አመት በፊት ሚያዚያ 9 ቀን 1996 ነው የተመሰረተው።

እስከዳር ግርማ

ሚያዚያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply