ማንቸስተር ሲቲ ለአራተኛ ተከታታይ ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆነ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቸስተር ሲቲ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል። በሜዳው ዌስትሃምን ያስተናገደው ሲቲ ጨዋታውን 3 ለ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/AuOvc6ITzL6pPI9yRNDaDxbSNDomLjA6SiuGgw7aDr3AofomcuuTfC_eja-QYvI3haxQsM_7pLW6dSdj9osFZkHTZphdtS7HXXsJjBefewXth1uFF5-WhdM_NHgM0WgjflSJkI3Kh4SMLbB_ykEqHnu1glmoO2kNxEsoE-K5UewyrieoyBqkk849sJozm7XnE91Y7rd50Hb6UviWhT-blSsFtVPxWtydWV8VooHQGlaMvVLxOAcdNwQjdewvyvHPjkaChEgrvt-r1LumC58a43fMR4gjki_3QwafmFaubXABpYfLR7IPzTSqb8BTs-EP45tvt-bdSeBGbL47qCAGVw.jpg

ማንቸስተር ሲቲ ለአራተኛ ተከታታይ ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆነ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቸስተር ሲቲ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።

በሜዳው ዌስትሃምን ያስተናገደው ሲቲ ጨዋታውን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሊጉን ለአራተኛ ተከታታይ ጊዜ በማንሳት አዲስ ክብረወሰን አስመዝግቧል።

የድል ጎሎቹን ፊል ፎደን (ሁለት) እንዲሁም ሮድሪ አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ሲቲ በ91 ነጥቦች የሊጉ ሻምፒዮን ሲሆን አርሰናል በ89 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።

ለዋንጫው እስከ መጨረሻው ሳምንት የተፎካከረው አርሰናል ኤቨርተንን አሸንፏል።

ሊቨርፑል እና አስቶንቪላ የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን ሲያሳኩ ሉተን ታዎን ሼፊልድን እና በርንሌይን ተከትሎ ሦስተኛው ወራጅ ክለብ ሆኗል።

ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply