ማንችስተር ሲቲ የሊጉ መሪ ሆነ! ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ አራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/CUkv7O7Jn7Lm1FFRCeiZJ5HASPRI3_QztSyiAziZhdY_E_GSGvIG7nZItJRnCvvorz_ce9ykoZWyHEM3ko57GP1nXDSosI1sJr1IURJUVaOcAsONKyV6WJZH3iCwj7WDrozv9b9XgluYh7F4jBB5YeFu9qaFsC10Y49D5B-q89clgCk2_ubJtzrDO8Fh1Yznvi7z6tZYdEmsQG0Yhh9hMc9w4XrD8rjwiPt6twhKcRq74M2vBcYzGGkt5vpVhiAKGxs4jgQIVDiPvyOYwyoVYFs-r_JgSgJhHfN3vbKxYYpcAxq74Fx8QiuJ9VHLZEKR5J3u0UACYLTRnxEdcU2qUg.jpg

ማንችስተር ሲቲ የሊጉ መሪ ሆነ!

ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ አራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት መረከብ ችለዋል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኬቨን ዴብሮይን አንድ መቶ አስራ ሁለተኛ ለግብ የሆነ ኳሱን አመቻችቶ በማቀበል በሊጉ ታሪክ ብዙ አመቻችቶ ያቀበለ ሁለተኛው ተጨዋች ሆኗል።

ኖርዊያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ ሀያ ሰባተኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ በአዲሱ የቶተንሀም ስታዲየም የመጀመሪያ የፕርሚየር ሊግ ጎል ማስቆጠር ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ :- 88 ነጥብ
ቀጣይ ጨዋታ 

እሁድ – ማንችስተር ሲቲ ከ ዌስትሀም ዩናይትድ

Source: Link to the Post

Leave a Reply