ማንችስተር ሲቲ ድል ቀንቶታል!

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከብራይተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ፊል ፎደን 2x ፣ ኬቨን ዴብሮይን እና ጁሊያን አልቫሬዝ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ፊል ፎደን በውድድር ዘመኑ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች አስራ ስድስት ማድረስ ችሏል።

ፊል ፎደን በዘንድሮው የውድድር አመት ለማንችስተር ሲቲ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው ጨዋታዎች በሰላሳ አራት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።
በቀጣይ ማንችሰተር ሲቲ ከ ኖቲንግሃም ጋር የሚገናኙ ይሆናል::

በጋዲሳ መገርሳ

ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply