ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ድል አድርገዋል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሰላሳ አራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ኮቢ ማይኖ ፣ አማድ ዲያሎ እና ራስሙስ ሆይሉንድ ሲያስቆጥሩ ለኒውካስል ዩናይትድ አንቶኒ ጎርደን እና ሀል አስቆጥረዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአንድ የውድድር አመት ሰማንያ አራት ግቦች ሲቆጠሩባቸው ከስልሳ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

በሊጉ

7 ኒውካስል ዩናይትድ :- 57 ነጥብ

8 ማንችስተር ዩናይትድ :- 57 ነጥብ

ቀጣይ

እሁድ – ብራይተን ከ ማንችስተር ዩናይትድ

ቼልሲ ከብራይተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ኮል ፓልመር እና ክርስቶፈር ንኩንኩ ከመረብ ሲያሳርፉ ለብራይተን ዳኒ ዌልቤክ አስቆጥሯል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ኮል ፓልመር በውድድር አመቱ ሀያ ሁለት የሊግ ግቦች አስቆጥሮ አስር አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

በጨዋታው እንግሊዛዊው የቼልሲ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሬስ ጄምስ ቀይ ካርድ የተመለከተ ሲሆን በዚህም ምክንያት የቀጣይ አመት የመጀመሪያ ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ያመልጡታል።

በሊጉ
6 ቼልሲ :- 60 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ
እሁድ – ቼልሲ ከ በርንማውዝ

በጋዲሳ መገርሳ

ግንቦት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply