ማንችስተር ዩናይትድ  የኤፌ ካፕ ሻምፒዮን ሆኗል ! ማንችስተር ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆናቸውን አ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/pqFuOn6-psXia_Wdzj1H8zuMiQhI3M3xCTSgUhDUVgYlDWDNrz9tTJpnJ3M_BhWT5KlBrWbAfD_Eoa16RDZ92OONIqetl0OFqfZBaI_LE-VHixD6Lus0CpJGVj_hLYVmVRo8gLFhcX0CMeqR4ZzRaqQxq8tRzPNWIEDjvJ3mm1xhvZX0AwjeC2mzjtQNTLeTcxyDHax0548c75fErx7C9NsB6FfqXoUUvtaRoRrPJDZWKcKSc_w-K9vV0JS01NT7-60OouJs0jfwHBCcdzmwIAwn6VBEm5cY7tFzM0OEhN4y7Eh2PRhVZneYRS9LQVWUYf_Mp96UWON_gPjHsES9_w.jpg

ማንችስተር ዩናይትድ  የኤፌ ካፕ ሻምፒዮን ሆኗል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በጨዋታው የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች አሌሀንድሮ ጋርናቾ እና ኮቢ ማይኖ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ጄርሚ ዶኩ ለማንችስተር ሲቲ አስቆጥሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ በታሪኩ ለአስራ ሶስተኛ ጊዜ የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ውድድር አሸናፊ መሆናቸውን ማረጋገጥ ችለዋል።

በክለቡ የወደፊት ቆይታቸው ያልተረጋገጠው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድን እየመሩ ሁለተኛ ዋንጫቸውን አሳክተዋል።

በሚቀጥለው የ2024/25 የውድድር አመት በአውሮፓ መድረክ የሚሳተፉ የእንግሊዝ ክለቦች ከምሽቱ የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በኋላ ተለይተው ታውቀዋል።

በዚህም መሰረት :-

– ሻምፒየንስ ሊግ :- ማንችስተር ሲቲ ፣ አርሰናል ፣ ሊቨርፑል እና አስቶን ቪላ

– ዩሮፓ ሊግ :- ማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሀም

– ኮንፈረንስ ሊግ :- ቼልሲ

ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ቼልሲ በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ በኮንፈረንስ ሊግ መሳተፍ የሚያስችላቸውን እድል ሳያገኙ ቀርተዋል።

በ ጋዲሳ  መገርሳ

Source: Link to the Post

Leave a Reply