“ማንነት ሁልጊዜ ከራስህ ጋር የሚቀበር ነው” የራያ አላማጣ ነዋሪዋች! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአላማጣ ከተማ የ…

“ማንነት ሁልጊዜ ከራስህ ጋር የሚቀበር ነው” የራያ አላማጣ ነዋሪዋች! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአላማጣ ከተማ የሚኖሩ የሃይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ከተማዋ ከትህነግ ቡድን ነፃ ከወጣ በኋላ የተሰማቸውን ስሜትና ሃሳብ በጋራ በመሆን በከተማዋ አዳራሽ ውይይት አድርገዋል፡፡ በወይይቱም የትህነግ አረመኔ ቡድን በአማራ ልዩ ሃይል በአማራ ሚሊሻ እና በሀገር መከላከያ ሰራዊት የተባበረ ሀይል ከአካባቢዉ እንዲወጡ መደረጉ ታላቅ እፎይታ ፈጥሮላቸዋል፡፡ ነዋሪዎቹ አያይዘዉም አሁን ያገኙትን ነፃነት ለማስቀጠል በኃይል የተቀሙትን ባህላቸውንና ታሪካቸውን የፌደራል መንግስት ወደ ነበረው የአማራ ማንነታቸው እንዲመልስላቸው ጠይቀዋል፡፡ በከተማ የሚገኙ የሁሉም ሀይማኖት ተከታዮች አሁን ለመጣው ሠላም ህይወታቸውን ላጡ ፀጥታ ሀይሎች በጋራ በመሆን በፀሎት አስበዋል፡፡ መረጃው የሰሜን ወሎ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply