ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በአዲስ አበባ! ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 24/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ዜጎች ማንነት ተኮር ግፍ እየተፈጸመብ…

ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በአዲስ አበባ! ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 24/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ዜጎች ማንነት ተኮር ግፍ እየተፈጸመብን ነውና በአስቸኳይ ይቁም ሲሉ ተናገሩ። ጎሮ፣ ቦሌ፣ ገርጅ ፣ ሮባ፣ ላምበረት፣ሳልተ ምህረት፣የረርና ሌሎች አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተለያዩ ሱቆች፣ ግሮሰሪዎች፣ ቡቲኮች ያሏቸው ዜጎች ማንነት ተኮር ጥቃት ተፈጸመብን፣ ሰበብ እየተፈለገ ሱቆቻችን እየተዘጉ ነው ሲሉ አማረሩ። በተጨማሪም ወጣቶች በለበሱት ቲሸርት የሚጠየቁበት፣ የሚሳደዱባት ከተማ መሆኗ እያደር እየከፋ ሄዷል ሲሉ ለዚህ ከፍተኛ የመብት ጥሰት ሰለባ የሆኑ ወጣቶች ተናገሩ። “መንግስት ይህ ችግር እያደገ ሲሄድ ዝም ብሏል። የከፋ ደረጃ ላይ ሳይደርስ በቃ ሊባል ይገባል። ማንነታችን ይከበር” ሲሉ እነዚህ ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ነዋሪወች አሳውቀዋል። እነዚህ የንግድ ሱቆቻቸው የተዘጉባቸው ነዋሪዎች አፋጣኝ መፍትሄ ይሰጠን ሲሉም ጠይቀዋል። አዲስ አበባ ውስጥ የማንንት ተኮር ጥቃት መፈጸም ለዚህች የሁሉ እናት ለሆነች ከተማ አደገኛ አካሄድ ነውና ሁላችን ልንታገለው ይገባል። አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ተጠቃሚም፣ ተለይቶ የሚጎዳም ዜጋ አይኖርም። በከተማችን እኩልነት ይስፈን። © ባልደራስ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply