You are currently viewing ማንንም አንነካ ማንም እንዲነካን ደግሞ አንፈቅድም፤ የማንንም አንፈልግም፤ ማንም ደግሞ መጥቶ እንዲወስድብንም አንፈልግም!”  ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…  ታህ…

ማንንም አንነካ ማንም እንዲነካን ደግሞ አንፈቅድም፤ የማንንም አንፈልግም፤ ማንም ደግሞ መጥቶ እንዲወስድብንም አንፈልግም!” ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህ…

ማንንም አንነካ ማንም እንዲነካን ደግሞ አንፈቅድም፤ የማንንም አንፈልግም፤ ማንም ደግሞ መጥቶ እንዲወስድብንም አንፈልግም!” ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ “ከዚህ በኋላ አማራን የሚደፍር ኃይል መኖር የለበትም” ያሉት ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው ፋኖ “ማንንም አንነካ፤ ማንም እንዲነካን ደግሞ አንፈቅድም፤ የማንንም አንፈልግም፤ ማንም ደግሞ መጥቶ እንዲወስድብንም አንፈልግም!” የሚል የአካሄድ መርህን እንደሚከተል ተናግረዋል። ጥር 1 ቀን 2014 ይመረቃሉ የተባሉትን በስልጠና ላይ ያሉ የሸዋ ፋኖዎችን በደብረ ብርሃን ከተማ ተገኝተው ከጎበኙት መካከል አንዱ የሆኑት ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ “ነፍሳችሁን አሲዛችሁ የአማራን ህዝብ ማንም ሊነካው አይገባም፤ ሸዋ ሊደፈር አይገባም፤ ወደ ቀደመ ክብራችን መመለስ አለብን” ብለው በመሰልጠን ላይ ጀግኖችን አመስግነዋል። “በክብር እና በጀግንነት ልክ እንደ አያቶቻችን ፋኖ በጀብድ እንደሚፎካከሩት ለመፎካከር እየተዘጋጃችሁ ያላችሁ ልጆች ስለሆናችሁ የእኛ አስተዋጽኦ በጣም ትንሽ ነች፤ የአማራ ህመም ያመናል፤ በደሉ ያመናል።” ሲሉም ተደምጠዋል። “መሰልጠን ሁልጊዜ መሰልጠን፣ ሁልጊዜ መሰልጠን፣ ሁልጊዜ መደራጀት፣ሁልጊዜ መታጠቅ በጣም ያስፈልጋል፤ ይህ ደግሞ በአመራር ሲታጀብ፣ በዲሲፒሊን ሲታጀብ ውጤት ያመጣል ብለን እናስባለን” ሲሉም አክለዋል። ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ ሲቀጥሉ “ይህንን ለማገዝም ሁሌም ከጎናችሁ ነን፤ በርቱ፤ ዛሬ ስላየኋችሁ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል፤ በምርቃታችሁ ቀን ለመገኘት ቃል እገባለሁ” ብለዋል። በተመሳሳይ ሌላኛው በስፍራው ተገኝተው ሰልጣኝ ፋኖዎችን ያበረታቱት ደግሞ አቶ ጌታሁን ይባላሉ፤ “በእናንተ ፈገግታ ውስጥ ኢትዮጵያ አለች፤ በጣም አንድ መሆን ይጠይቃችኋል፤ ይጠይቀናል” ሲሉ መክረዋል። “በተቻለ መጠን በሀሳብ በምንችለው ሁሉ ከጎናችሁ ነን፤ እናንተ ልጆች ናችሁ፤ ገና ወጣት ተስፋ ያላችሁ ናችሁና ሀገራችን የሚፈለገውን ያህል የምታድገውም በእናንተ ነው” ያሉት አቶ ጌታሁን ሸዋ ላይ እንዲህ ተሰብስባችሁ ከፊት ለፊት ስትመጡ እንደ አያታችሁ እንደ አምደ ጽዮን የሚፈራ ቀስተ ንብ የሆነ ወታደር እንደምትሆኑ ሙሉ እምነትም ተስፋም አለኝ፤ ህዝባችን በእናንተ ተስፋ ያደርጋል፤ እናሸንፋለን።” ነው ያሉት። በደብረ ብርሃን አባላትን ሲያሰለጥኑ ያገኘናቸው የሸዋ ፋኖ አሰልጣኞችና አስተባባሪዎችም ሰልጣኞችን ያስጎበኙ ሲሆን አሁን ያለን አማራጭ “አማራ ሁሉ ፋኖ ነው፤ ፋኖ ሁሉ አማራ ነው” የሚል መርህን እየተከተልን ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply