‹‹ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው!!!›› (ክፍል አንድ)-ሚሊዮን ዘአማኑኤል

‹‹ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ15 የሕይወት መብት

በኢትዮጵያ በህወሓት/ ኢህአዴግ የ29 ዓመታት ግፍ አገዛዝ ዘመን  ሰው በመግደል ወንጀል የሃያሎም አርዓያና የክንፈ ገ/መድህን ገዳዬች በገዳይ ስኮዶች በጥይት ተደብድበው ተረሽነዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የሞት ቅጣት ጊዜያዊ እገዳ ብሎም የሞት ፍርድ እንዲቀር ጥሪ ያደርጋል፡፡ በዓለማችን 106 አገራቶች 60 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የሞት ቅጣት ፍርድ በሌለበት ዓለም ይኖራሉ፡፡ ቀሪዎቹ 56 አገራቶች ደግሞ 40 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የሞት ፍርድ ባለበት ዓለም ውስጥ ይኖራል፡፡ የሞት ቅጣት በምድረ ቻይና፣ ህንድ፣ አሜሪካ፣ ኢንዶኔሽያ፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዲሽ፣ ናይጀሪያ፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ሳውዲ ዓረቢያ፣ ኢራን፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን፣ ሲሪላንካ ወዘተ ውስጥ ይገኛል፡፡ የጠቅላላ አገሮች የሞት ቅጣት ፍርድ ድምርን ቻይና ባቻዋን ታስከነዳቸዋለች፡፡ የሞት ቅጣት ፍርድ ዓይነቶች እንደ የአገራቶቹ ይለያያል፣ ስቅላት፣ አንገት መሠየፍ፣ መረሸን፣ በሌሰል የመርዝ ብልቃጥ ስሪንጅ በመርፌ መግደል፣ በኤሌክትሪክ ወንበር መግደል፣ በድንጋይ ወግሮ መግደል ወዘተ ይገኙበታል፡፡

“The United Nations General Assembly has adopted, in 2007, 2008, 2010, 2012 and 2014,[4] non-binding resolutions calling for a global moratorium on executions, with a view to eventual abolition.[5] Although most nations have abolished capital punishment, over 60% of the world’s population live in countries where the death penalty is retained, such as China, India, the United States, Indonesia, Pakistan, Bangladesh, Nigeria, Ethiopia, Egypt, Saudi Arabia, Iran, among all mostly Islamic countries, as is maintained in Japan, South Korea, Taiwan, and Sri Lanka.[6][7][8][9][10] China is believed to execute more people than all other countries combined.[11]… Fifty-six countries retain capital punishment, 106 countries have completely abolished it de jure for all crimes, eight have abolished it for ordinary crimes (while maintaining it for special circumstances such as war crimes), and 28 are abolitionist in practice.[2]

የሞት ቅጣት ፍርድ ወንጀል ተፈፃሚነት፣ በተለያዩ መንግሥታት በፍርድ በግለሰብና በቡድን የተፈጸሙ ወንጀሎችን መሃከል የሰው ግድያ፣ የብዙ ሰዎች ግድያ፣ የሽብር ድርጊቶች፣ የአገር ክህደት፣ ስለላ፣ በመንግስትና ህዝብ ላይ የተፈፀመ የህግ ጥሰት፣ እንዲሁም የመንግሥት ግልበጣ መፈንቅለ መንግሥት ሴራ ውስጥ መሳተፍ፣ የዕፅ ዝውውር፣ የጦር ወንጀለኛነት፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ እና የዘር ፍጅት እንዲሁም የተለያዩ የህግ ጥሰቶችን ጨምሮ የተጠረጠረ ግለሰብና ቡድን በመንግሥት ፍርድ ቤት ቀርበው ፍርድ ሲሰጣቸው እናያለን፡፡

“Crimes that are punishable by death are known as capital crimes or capital offences, and they commonly include offences such as murder, mass murder, terrorism, treason, espionage, offenses against the State, such as attempting to overthrow government, piracy, drug trafficking, war crimes, crimes against humanity and genocide, but may include a wide range of offences depending on a country….

በ2018 እኤአ በዓለም በሚገኙ አምስት አገሮች የተፈፀሙ ግድያዎች  ዝርዝር ውስጥ ቻይና መንግሥት 1000 በላይ ወንጀለኞች ገድሎል፣ኢራን መንግሥት 253 በላይ ወንጀለኞች ገድሎል፣ሳውዲ አረቢያ መንግሥት 149 ወንጀለኞች ገድሎል፣ ቬትናም መንግሥት 85 በላይ ወንጀለኞች ገድሎል፣ኢራቅ መንግሥት 52 በላይ ወንጀለኞች ገድሎል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ የሞት ቅጣት ፍርድ የሚፈፅመው በጥይት ደብድቦ በመግደል መረሸን እንደሆነ የሽምቅ ተዋጊ በነበሩበት ጊዜም የሚጠቀሙበት ቅጣት ነበር፡፡ እንደ ኮርኔል የዓለም አቀፍ የሞት ቅጣት ማዕከል (Cornel Centre on the Death Penalty Worldwide) ጥናት መሠረት  በኢትዮጵያ እስከ 2013 እኤአ ድረስ 120 የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሰዎች ቅጣታቸውን እንደሚጠባበቁ ይገመታል፡፡   በ2012 እኤአ በኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩት 111,050 (መቶ አስራአንድ ሽህ ሃምሳ) እስረኞች ውስጥ  15 በመቶዎቹ የፍርድ ሂደት የሚከታተሉ ገና ያልተፈረደባቸው የቀጠሮ እስረኞች ነበሩ፡፡ በሃገሪቱ የክልል መንግሥቶች በሚገኙ 120  እስርቤቶች ውስጥ የታሰሩ የነበረ ሲሆን እንዲሁም በፌዴራል መንግሥቱ ስድስት እስርቤቶች እንደነበሩ ጥናቱ አስታዎቆል፡፡  (Ethiopia’s Dilemma with Capital Punishment, Long Overdue (ADDISFORTUNE)

)ሕወሓት ሙሉ ለሙሉ በዓድዋ ተወላጆች ቁጥጥር ስር የዋለው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ‹‹ህወሓት በመጀመሪያ ከሩቅ ሲያዩት ፤ብሔርተኛ ይመስላል፡፡ ትንሽ ጠጋ ስትለው ፣ጎሰኛ ይሆናል፡፡ አሁንም ጠጋ ስትለው ፣ ጎጠኛ ይሆናል፡፡ ይበልጥ ጠጋ ስትለው ፣ መንደርተኛ ይሆናል፡፡ በመጨረሻ ከጎኑ ስትቆም ፣በዘረኝነት የናወዘ የጥቅም ሱሰኛ መሆኑ ይገለጥልሃል!!! ያን ጊዜ አሁን ሙያ የመሠለህ የዘውግ፣ብሔርተኝነት ኢ-ስብዓዊ የሆነ የዱኩማኖች አመለካከት እንደሆነ ይገባሃል፡፡ የሰው ልጅ የክፋት ጥጋት ከዚህ የአመለካከት ጥበት ውስጥ መሆኑ በግልፅ ይታይሃል፡፡ ያኔ መንግሥትና ፓርቲ ቀርቶ ሰው መሆንህ በራሱ ያስፈራሃል!!!›› -(ስ.ተ)

በኢትዮጵያ በህወሓት/ ኢህአዴግ የ28 ዓመታት የግፍ አገዛዝ ዘመን  ሰው በመግደል ሁለት ወንጀለኞች ብቻ በጥይት በገዳይ ስኮዶች ተረሽነዋል፡፡ ሆኖም በህወሓት ቅፅበታዊ ፍርድ በገዳይ ስኮዶችና የአጋዚ ጦር በየመንገዱ ላይ  አሰፋ ማሞ ገድለዋል፣ በየሰላማዊ ሰልፍ ላይ አዲስ አበባ፣ አዋሳ፣ ጋምቤላ ሃረር፣ ቦረና፣ ብሸፍቱ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ደሴ፣ ወዘተ የተረሸኑ ብዙ ሽህ ወጣቶች ቤቱ ይቁጠራቸው እንላለን፡፡ የህወኃት ገዳዬቹ ከህግ አምልጠው መቀሌ መሽገዋል፡፡

በህወሓት የውክልና ጦርነት በተለይ በሶማሌ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በአማራ ክልል፣ አሰቃቂ ግድያዎች  በተለይ የመንጋ ፍርድ፣ የጀማ ፍርድ እንዲሁም አሰቃቂ ኢስብዓዊ ግድያ በገጀራ፣ በጦር፣ በድንጋይ፣ በዱላ ወዘተ ሰውን ጨፍጭፎ መግደል ለማስቆም መንግሥት የህግ የበላይነትን በማስከበር የሞት ቅጣት  አተገባበር ላይ ውይይት ቢከፈት የመንጋ ፍርድ አድራጊዎች በየዩኒቨርሲቲዎቹና በየክልሎቹ ወዘተ ገዳዬች ከዚህ ድርጊታቸው ሊቆጠቡና ሊቆም ይችላል የሚሉ በአንድ ጎራ ይሞግታሉ፡፡

 • የሞት ፍርድ መተግበሩ በተለይ በኢስብዊ መንገድ በገጀራ፣ በጦር፣ በድንጋይ፣ በዱላ ወዘተ በቡድን የሚፈጸሙ ግድያዎች ድርጊት ፈፃሚዎች በህግ እንዲጠየቁና፣ ታድነው ተይዘው ለፍርድ ሲቀርቡ ከታየ በሌላ ቦታዎች ተመሳሳይ ወንጀሎች ይቀንሳሉ ብሎም የደቦ ግድያው ይቆማል፡፡
 • በኢትዮጵያ በሚገኙ ክልሎች ውስጥ በስጋት የሚኖሩ ሰዎች ‹‹መጤና ነባር›› ተብለው የተፈረጁ የህግ ዋስተና ያጡ ኑዋሪዎች ይህ ህግ ተፈፃሚ ካልሆነ በሚቀጥሉት ጥቂት ጊዜት ውስጥ የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ይሆናል እንላለን፡፡ የዳክተር አብይ መንግሥት የህግ የበላይነትን መተግበር ባለመቻሉ የተነሳ ብዙ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፣ ልጃገረድ ሴቶችና እናቶች ተደፍረዋል፣ ሃብትና ንብረታቸው ተዘርፎል፣ ህጻናትና ወጣቶች የሥነ ዓዕምሮ ቀውስ ተዳርገዋል እስከ 3 ሚሊዮን ህዝብ በመላ ሃገሪቱ ተፈናቅለዋል፡፡
 • የዳክተር አብይ መንግሥት የህግ የበላይነትን መተግበር ካልቻለ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመላ ሃገሪቱ ተዘዋውሮ መሥራት ካልቻለ፣ ሃብትና ንብረት ማፍራት መብት ከሌለውና በህግ ፊት እኩል ካልሆነ፣ ‹‹ጨዋታው ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ›› ተባብለን ወደ ዘር ስልቻችን በመታቆር፣ ‹‹የመጤና ነባር›› ትርክትን አስፈፃሚው በሰላም መጤውን ህዝብ ከሙሉ ክብሩ ወደ ክልሉ ማሰናበት ይኖርበታል፡፡ የሕወሓት ህገመንግሥት በህግ ሊሻርና አዲስ ህገመንግሥት ሊረቅ ይገባል እንላለን፡፡
 • ተፈናቃይ ህዝብ ዳግም ወደ መጡበት መልሶ የማስፈር እርቀ ሰላም የሚለው ፈሊጥ በተደጋጋሚ ለተፈናቃዮች ሞትና ስደት የዳረገ በመሆኑና ተፈናቃዬች ከገዳዬቻቸው ጋር እንዲኖሩ በመገደዳቸው ለከፍተኛ የሥነ አይምሮ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቀው በእውሸት እርቅ፣ ፍትህ ባልተሰጠበት፣ ፍርድ ባልተገኘበት ሁኔታ አንዱን ጠቅሞ፣ ሌላውን ጎድቶ የሚደረግ የይስሙላ የሽምግልና እርቅ በተደጋጋሚ ለብዙ ሰዎች እልቂት ምክንያት ሆኖል፡፡ በሁሉም ክልሎች የህግ የበላይነት ተፈፃሚነት ካላገኘ እርቀ ሰላሙ የውሸትና ከንቱ ነው መንስዔው መቅኒው ድረስ የዘለቀ የድህነት አረንቆ ውስጥ ህብረተሰቡ በመኖሩ የተነሳ የመጤውን መሬት ለመንጠቅ፣ ከብቶቹን ለመንዳት፣ ገንዘቡን ለመንጠቅ፣ ሴቶቹን ለመድፈር፣ ወዘተ መሆኑን አለመረዳት ለብዙ ሰዎች እልቂትን ያስከትላል እንላለን፡፡
 • አሰቃቂ ኢስብዓዊ ግድያ የፈፀሙ ወንጀለኞች በገጀራ፣ በጦር፣ በድንጋይ፣ በዱላ ወዘተ የጅምላ ግድያ ድርጊት የፈጸሙ በሃገሪቱ ህግ መሠረት ያለው የሞት ፍርድ ቢቻል በአደባባይ በገበያ መኃል ወንጀለኞችን በመስቀል የሰው መግደል ወንጀል እንደሚያስቀጣ ህብረተሰቡ ካልተረዳ በውሸት እርቀ ሰላም አይፈታም እንላለን፡፡
 • ህወሓት በአለፉት 29 አመታት በአደባባይ ሰው በስናይፐር አድኖ የሚገድል አውሬ በአደባባይ መሰቀል ሲያንሰው ነው፣ ያን ለበቀል ሳይሆን የህግ የበላይነትን በመላ ሃገሪቱ ያጠፋ፣ ወንጀለኞች ገድለው የሚኖሩበት የሽፍታ የከተማ መንግሥት ባህል ያስፋፉ በመሆናቸው ዛሬ በየቦታው የተከሰተው ወንጀለኛነት የተስፋፋው ለገዳዬች ፍርድ ሥለማይሰጥ፣ ለፍርድ ስለማይቀርቡና ከገዳዬቻችንና ከገራፊዎቻችን ጋር አብረን እየኖርን ስለሆነ በፍርሃት ቀንበር ስር ህብረተሰቡ ይኖራል፡፡

The death penalty – the arguments for and against/

In some countries it is legal to kill someone if they have committed a terrible crime. This is called a death sentence, or the death penalty. It is not legal in Britain.

There are lots of reasons why people think it’s right or wrong. Here are some of the arguments:

የሞት ፍርድን በመደገፍ የሚቀርቡ ክርክር ውስጥ፡-

·         አንድ ሰው የሌላውን ሰው ከገደለ፣ የሞችን ስብዐዊ የመኖር መብት ተጋፍቶል፣ እንዲሁም  በህይወት የመኖር መብትን በመጣሱ

·         ቅጣቱ ‹ከወንጀሉ ጋር የተመጣጠነ› ሰው ከገደልክ አንተም ትገደላለህ

·         የገዳዬችን በሞት መቅጣት ሞትን ማስቆም ይቻላል፣ ሌሎች ሰው እንዳይገሉ ያደርጋል

·         ወንጀል የፈጸመ ሰው መግደል ለማህበረሰቡ ውስጥ ሌላ ገዳይ እንዳይፈለፈል ይረዳል በማለት ይሞግታሉ፡፡

Arguments for the death penalty

 • If someone murders someone else, they have given up their human rights, including the one to stay alive themselves
 • The punishment should ‘fit the crime’ – if you have killed someone, you should be killed too
 • Giving a killer the death sentence will stop them – and others – doing it again
 • The very small chance of executing the wrong person is balanced by the benefits to society of putting off other murderers

የሞት ፍርድን በመንቀፍ የሚቀርቡ ክርክር ውስጥ፡-

·         የሞት ፍርድ ቅጣት፣ የሞችን ስብዐዊ የመኖር መብት ይጋፋል፣ የሰውን በህይወት የመኖር መብትን ይጥሳል

·         የሞት ቅጣት ፍርድ ዓይነቶች እንደ የአገራቶቹ ይለያያል፣ በሌሰል የመርዝ ብልቃጥ ስሪንጅ በመርፌ መግደል፣ በኤሌክትሪክ ወንበር መግደል፣ ወይንም ስቅላት፣ አንገት መሠየፍ፣ መረሸን፣  በድንጋይ ወግሮ መግደል ወዘተ  ስቃዩና ህመሙ ከፍተኛ ነው  ሰዎቹ ተሰቃይተው ነው የሚሞቱት ፡፡

·         በሞት ፍርድ ቅጣት፣ ወንጀለኞችን መግደል ሌላ ግድያዎችን አያስቆምም ይሄንንም በማስረጃ በቁጥር ማቅረቡ አይቻልም፡፡

·         አንዳንዴ በህግ ስህተት የሞት ፍርድ ቅጣት የተፈረደበት  ሰው ንፁህ ሰው ሆኖ ይገኛል፡፡ ያለኃጢያቱ  መገደሉ ሞችን አይመልሰውም፡፡

Arguments against the death penalty

 • The death penalty goes against our most basic human right – the right to life
 • Being killed by lethal injection or being electrocuted is not always smooth and painless, sometimes it causes a painful death
 • No-one has ever proven with numbers that killing murderers stops other people committing similar crimes
 • Mistakes are sometimes made in the law – what if someone is killed who is actually innocent?

‹‹ገዳይን በመግደል ሞችን አያስነሳም››

“Killing killers won’t bring back victims”

‹‹ለምን ሰዎን የገደለን ሰው ትገለዋለህ፣ ሰውን መግደል ስህተት ከሆነ!››

“Why do we kill people who kill people to show that killing people is wrong?”

‹‹የሰው ህይወት ከቀጠፍክ፣ የአንተም ህይወት ይቀጠፋል ››

“If you take lives, yours can be taken”

በቻይና መንግሥት የሞት ቅጣት ለሚጠብቃት ኢትዮጵያዊት የንፁህ አምላክ፣ሽህ በክንፉ፣ ሽህ በአክናፉ ይጠብቃት!!! መንግሥትና ህዝብ ይታደጋት!

መተንፈስ አልቻልኩም!!! መኖር አልቻልንም!!!

መሪ ከሆንክ ‹‹ ብዙ ሥራ፣ ትንሽ ተናገር›› “Leaders should do more and speak less” ዲንግ ሲያኦፒንግ የቻይና መሪ የነበሩ፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ መተንፈስ አልቻልንም!!! መኖር አልቻልንም!!!  በዚህ ምድር ላይ መጤ ተብለን መገደል ሰለቸን!!!  በዚህ ዓለም ሁላችንም  መጤ መሆናችንን ረሳን፡፡ ከቦታ ቦታና ከሥፍራ ሥፍራ ተዘዋውረን መሥራትና ኃብት ማፍራት አልቻልንም፡፡ መንግሥትዎ ‹‹ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው!!!›› የሚለውን ህግ ብቻ እንዲያስከብር እንጠይቃለን፡፡ የፌዴራል መንግሥትዎ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ፖሊስ ሠራዊት፣ አየር ኃይል፣ ዓየር ወለድ፣ የፀጥታና ደህንነት ቢሮ  እችን አንድ ህግ ብቻ እንዲያስከብር እንጠይቃለን!!!

 • ማንኛውም ሰው ስብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር ፣የአካል ደህንነትና፣ የነጻነት መብት አለው፡፡ የሕይወት፣ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት፣ አንቀጽ 14
 • ‹‹ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው!!!›› የሕይወት መብት፣ አንቀፅ 15
 • ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርሰበት የመጠበቅ መብት አለው ፡፡ የአካል ደህንነት መብት፣አንቀጽ 16
 • በህግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ማንኛውም ሰው ወንድም ሆነ ሴት ነፃነቱን/ቷን አያጣም/ አታጣም ፡፡የነፃነት መብት ቁ. 1 አንቀጽ 17
 • ማንናውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ሊያዝ፤ ክስ ሳይቀርብበት ወይም ሳይፈረድበት ሊታሰር አይችልም፡፡ የነፃነት መብት ቁ. 2 አንቀጽ 17

 

ምንጭ

(1) Capital punishment/ From Wikipedia, the free encyclopedia

(2) Ethiopia’s Dilemma with Capital Punishment, Long Overdue (ADDISFORTUNE)

(3) The death penalty – the arguments for and against/ 21 Sep 201121 September 2011

 

Leave a Reply