ማእከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኘውን ጎርጎራ ለቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ በነበረበት የህግ ማስከበር ዘመቻው እንቅፋት የፈጠረ ቢሆንም ዲዛይኑ ተጠናቆ የትግበራ ስራው ከ10 ቀናት ቡሃላ እንደሚጀመር ተገለፀ ፡፡

በማእከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኘውን ጎርጎራ ለቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ በነበረበት ወቅት የህግ ማስከበር ዘመቻው እንቅፋት ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ዲዛይኑ ተጠናቆ የትግበራ ስራው ከ10 ቀናት ቡሃላ እንደሚጀመር ተገለፀ ፡፡

የማእከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ሀይለማሪያም ለአሀዱ እንደገለፁት ጎርጎራን ለመስህብነትና የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ትልቅ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝና በርካታ ባለሃብቶችም ፕሮጀክቶችን ይዘው የአብረን እንስራ ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛሉ ብለዋል ፡፡

አክለውም ጎርጎራን ለቱሪዝም መዳረሻ ለማድርግ እየተሰራ በነበረበት ወቅት በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ እንቅፋት ፈጥሮ ቆይቷል፡፡ አሁን ላይ ግን በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝና ዲዛይኑ ተጠናቆ የትግበራ ስራው ከ 10 ቀናት ቡሃላ እንደሚጀመር ዋና አስተዳዳሪው ገልፃል፡፡

በተጨማሪም በዚያው ቀጠና የሚገኙ ቅርሶች  ለቱሪስቶች ክፍት ሆነው እንዲጎበኙ በማድረግ ለዘርፉና ለሀገሪቱ ገቢ እንዲያስገኙ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ቀን 15/06/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply