ማክሰኞን ለምስጋናው…በፌስቡክ ላይቭለበርካታ ዓመታት በስፖርት ጋዜጠኝነት የሰራውና የሙያ ባልደረባችን የሆነው ምስጋናው ታደሰ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በጠነከረበት ህመም ምክንያት ብዙ ዋጋ ከ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/uvq-vVmYmLRnEwoKSz8Hj-vwBAs0YT-LY5bbxZJn37JT11xv-hDomQUtKZVkN1u_SOL-msyXSpBv2x_I3gJUEmOKX0q2epB1GyA4O5KSXuv63mOFfo2iqgNz9o4MOVpHJYY9PhvUvG7Mc2b0oedw5q8FY_UH35YceA-7VPOaTnHLERaLa5dtrSJmhFBlB_D1T2y6_S4YYHn8Qe8ClOLrf9Gl9RFmcQB1MPjXQU6qKh5KMma4eVzd8Rh1fZuYZKqrh3ibKbrOnVqSyrMkPn1YCPjsuTpIOZ4rEPAUaNlJVI3PYRoDCQV3UXNazhXKEuOQuC_XatccN79srerd0XHn_A.jpg

ማክሰኞን ለምስጋናው…በፌስቡክ ላይቭ

ለበርካታ ዓመታት በስፖርት ጋዜጠኝነት የሰራውና የሙያ ባልደረባችን የሆነው ምስጋናው ታደሰ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በጠነከረበት ህመም ምክንያት ብዙ ዋጋ ከከፈለለት የስፖርት ጋዜጠኝነት ሙያ እና ጤናው እየተፈተነ ይገኛል። ህመሙ በርትቶበት ሆስፒታል ለመተኛት ተገዷል

ጋዜጠኛ ምስጋናው ጤናው ተመልሶ ወደሚወደው ሙያ እንዲመለስና አሁን ህመሙ ከደረሰበት ደረጃ እና በፍጥነት አስፈላጊውን የህክምና ክትትል አግኝቶ ከህመሙ እንዲያገግም የሁላችንም ከፍተኛ ትብብር የሚፈልግበት ጊዜ ደርሷል።

ቀደም ሲል ከተገለፀለት የነርቭ እና ዲስክ ህመም በተጨማሪም የተጓዳኝ ህመሞች( ማለትም ኩላሊት እና ልብ) ህመም ስጋት እንዳለበት ተነግሮታል።

ይህን የድጋፍ ጥሪ በማስተባበሩ ረገድ ጋዜጠኛ ነዋይ ይመር፣ ጋዜጠኛ ኑራ ኢማም እና ጋዜጠኛ ስዮም ፍቃዱ ኃላፊነቱን በመውሰድ ኮሚቴ በማቋቋም በስማቸው አካውንት ተከፍቷል።

ኮሚቴው በተለያዩ መንገዶች ገቢ ለመሰብሰብ ያሰበ ሲሆን ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 12/2016 ከሰዓታት በኃላ ከምሽቱ 12:30 ጀምሮ በ #TamiruAlemu የፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ገቢ ለመሰብስብ ታስቧል።

እርሶዎም በዚህ የበጎ አድራጎት ስራ ላይ እንዲሳተፉ በአክብሮት እንጋብዞታለን። በኮሚቴው አባላት ጋዜጠኛ ነዋይ ይመር፣ ኑራ ኢማምና ስዩም ፍቃዱ ስም በተከፈተው በቀጣዩ የባንክ አካውንት የበኩልዎን ድጋፍ ያድርጉ፡፡

1000605343604 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Source: Link to the Post

Leave a Reply