ማዕድን ሚኒስቴር 972 ፈቃዶችን መሠረዙን አስታወቀ

የ116 ኩባንያዎች የማዕድን ፍለጋ ፈቃዶች ተሠርዘዋል

ዕረቡ ሰኔ 15 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የማዕድን ሚኒስቴር የማዕድናት ፍለጋ ፈቃድ ወስደው ለረጅም ጊዜያት በገቡት ውልና አቅርበው ባፀደቁት መርሀ ግብር መሠረት መስራት ባልቻሉ ኩባንያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

ኩባንያዎቹ ሚኒስቴሩን ጨምሮ በየደረጃው ባሉ ባለድርሻዎች ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም በሚገባው መልኩ ወደ ልማት ባለመግባታቸው የ116 ኩባንያዎች የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ መሠረዙን የማዕድን ሚኒስትሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በማዕድናት ምርት ፈቃድ ወስደው ነገር ግን በአግባቡ አልሰሩም የተባሉ የ6 ኩባንያዎች ፈቃድ ተሰርዟል ።

ከወርቅ ማዕድናት ውጪ ያሉ ሌሎች ማዕድናት ወደ ውጪ ለመላክ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ወስደው ፈቃድ የተሠጣቸው ነገር ግን፤ በህጋዊ ሽፋን በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ ተሠማርተው የተገኙ 850 የማዕድን ላኪዎች ፈቃድ መሠረዙን ሚንስትሩ ተናግረዋል ።

በአጠቃላይ 972 በማዕድን ምርመራ ፤ ምርትና ኤክስፖርት ዙሪያ ፈቃድ የወሰዱ ኩባንያዎች ፈቃድ ተሰርዟል መባሉን ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል።

በክልሎች በኩል የተሠጡ ፈቃዶች በዚህ ወር መጨረሻ ተገምግሞ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ከሥምምነት መደረሱም ተገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply