ማይክ ሃመር በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ፤

የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር ከትናንት ነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜ 3 ድረስ ከናይሮቢና ከአዲስ አበባ መንግሥታት ከአፍሪካ ህብረት፣ ከልማት ድርጅት ባለስልጣን እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ለመነጋገር እንዳቀኑ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ማስታወቁን የዲ ደብልዩ የአማረኛው ክፍል ዘግቧል።

ሐመር በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ቆይታ፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶች በድርድር እንዲቋጩ እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ እና ከለላ እንዲያገኙ ግፊት ያደርጋሉ ተብሏል።

ሐመር፣ በሱዳን ቀውስና ጦርነቱን ለማስቆም እየተደረጉ በሚገኙ ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጥረቶች ላይም ከአካባቢዉ አገራት፤ ከአፍሪቃ ኅብረትና ከኢጋድ መሪዎች ጋር እንደሚመክሩ ሚንስቴሩ አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply