You are currently viewing ሜሪይ ጆይ ኢትዮጵያ ደብረብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 25 ቀን 20…

ሜሪይ ጆይ ኢትዮጵያ ደብረብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 25 ቀን 20…

ሜሪይ ጆይ ኢትዮጵያ ደብረብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የሜሪይ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ እንደገለጹት ከዚህ በፊት መጥተው ባዩት ነገር በማዘናቸው ከሜሪ ጆይ በጎፈቃደኞች፣አርቲስቶችና በውጭ ከሚኖሩ ተባባሪ አካላት የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አሰባስበው መምጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ዛሬ የሰው እጅ ለመጠበቅ የተገደዱት ወገኖች ትላንት ብዙ ሀብት የነበራቸውና ሌሎችን ይረዱ የነበሩ በተፈጠረው ችግር ለአደጋ መጋለጣቸው አሳዛኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በተቆራረጠ መንገድ ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍም ለውጥ እንደማያመጣና መንግስት ዘላቂ መፍትሄ መፈለግ እንዳለበት አመልክተዋል፡፡ እስከዚያው ተባብረን ተፈናቃዮችን ልንረዳቸው ይገባል ብለዋል፡፡ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ተስፋየ ዘውዴ እንደገለጹት በሰው ሰራሽ ችግር ወገኖች ለአደጋ መጋለጣቸው ልብ የሚነካና የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡ በሀገራቸው ዜጎች በዚህ ደረጃ ችግር ውስጥ ወድቀው ማየት ልብ የሚነካ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአሜሪካና በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዮኒ ቬጋስ እንደገለጹት ባለፈው ሳምንት መጥተው ችግሩን በማየታቸው ሜሪጆይ፣አርቲስቶች፣ባለሀብቶች ተነጋግረው ድጋፍ አሰባስበው ይዘው መምጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡ አሁን ላይ ሳምንት ከነበረው የተፈናቃይ ቁጥር መጨመሩን መመልከታቸውን ጠቅሰው ችግሩን ለመቀነስ ሰው የሚፈናቀልበትን ምንጭ ማድረቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ መንግስት ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡ ሰውን ለመርዳት ብሄር፣ ዘር ወይም ሃይማኖት እንደማያግደው ጠቅሰው በችግር ውስጥ ያሉትን ዜጎች ተባብሮ መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ወደፊትም የሚያደርጉት ድጋፍ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ በተመሳሳይ በአሜሪካ ጆርጅያ ላስቬጋስ የሚኖሩት ወይዘሮ መስከረም ጌታቸው እንደገለጹት ለ3ኛ ጊዜ መምጣታቸውን አስታውሰው በካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች በተለይም ህፃናት ያሉበት ችግር በጣም አሳዛኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አርቲስት አብራር አብዶ አክለው እንደገለጹት ተፈናቃዮች ያላቸውን ሀብትና ንብረት አጥተው በችግር ውስጥ መሆናቸውን ጠቅሰው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በገንዘብ፣በቁሳቁስ፣በአልባሳት ድጋፍ እንዲያደርጉ በፈጣሪ ስም ጠይቀዋል፡፡ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ እታገኝ አደም ድጋፉን ሲረከቡ እንደተናገሩት መንግስት ሰፊ ድጋፍ እያደረገ ቢሆንም ከተፈናቃዮች ቁጥር ብዛት አንጻር ሁሉንም መድረስ ባለመቻሉ ክፍተቱን ለመሙላት ተባብራችሁ የወገኖቻችን ችግር ተሰምቷችሁ ድጋፍ ላደረጋችሁ አካላት ሁሉ በክልሉ መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል። በአማራ ክልል ሰፊና ውስብስብ ችግር መኖሩን ጠቅሰው በክልሉ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ክልሉ 3 ጊዜ ጦርነት የተካሄደበት በመሆኑ ከክልሉ ውጭና በክልሉ ውስጥ ብዙ ህዝብ መፈናቀሉን አመልክተዋል፡፡ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply