ሜድሮክ በ50 ቢሊየን ብር ለሚገነባው ዘመናዊ መንደር በዛሬው እለት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በመቻሬ ሜዳ በ50 ቢሊየን ብር በ250 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/rCTAK0YqyxmPEDO3PZirUaEP0uH_Pt_HvhJ7Y8QpA7F6UnQJutIW5Gs5XkGt30l30ZxFDjOpdbG0pMmT_a1qLK86q9TV6Dchet0Mf133qtw9AsdO2pedX4JQPjk8kZqlYhB2FwmEW00cD0ZI6Ogn74BrRJMPZ33qg-zSoLDLBCD6K_hPXZM_vmGO67S_JTOz21TTmTT72lELwf3NEEra_8DTkLAFOLYYHvjCVzRk1wBi6LNQcn4k6XcWJO8w3Nrot23C3L0nUKFr9tJCvDN5i6JbEF40-UxuRU1wU4Ffa317a5DXfuvosN-OE9PHh6ITz7I-M7FnTrmXa1xw8utVuA.jpg

ሜድሮክ በ50 ቢሊየን ብር ለሚገነባው ዘመናዊ መንደር በዛሬው እለት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በመቻሬ ሜዳ በ50 ቢሊየን ብር በ250 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ለሚያስገነባው ዘመናዊ የመሀመዲያ መንደር ነው የመሰረተ ድንጋይ ያስቀመጠው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመሰረተ ድንጋዩን አኑረዋል፡፡

ለመዲናዋ አዲስ ውበትን ይጨምራል የተባለው ይሄው ዘመናዊ የመንደር ግንባታ ከአምስት እስከ ሰባት አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

50 ቢሊዮን ብር ወጭ ይጠይቃል የተባለው ይህ ዘመናዊ መንደር እጅግ ዘመናዊ ሞል፣ የግብይት ማዕከላት፣የአረንጓዴ ቦታን፣አዲሱ ሆቴል፣ ቪላዎች፣ ፣ ሱፐር ማርኬት፣ አፓርትመንት፣ ለእግረኛ ምቹ የሆኑና መንገዶችና ሎሎችም መሰረተ ልማቶችን ያሟላና በአለምአቀፍ ስታንዳርድ መሰረት የሚገነባ መሆኑን ሰምተናል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጳጉሜ 05 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply