ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ጥሪ ቀረበላቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዛሬው ዕለት ጥቅምት 26 ቀን 2013 ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡
 
በትናትናው ዕለትም ከዚህ በፊት ከመከላከያ ሠራዊት ተቀንሰው የነበሩ ሦስት መኮንኖች ጥሪ እንደቀረበላቸው የሚታወስ ነው፡፡
 
ጥሪ የቀረበላቸው መኮንኖችም ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ፣ ሌ/ጄኔራል ዬሐንስ ገ/መስቀል እና ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

The post ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ጥሪ ቀረበላቸው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

Leave a Reply