ምርጫዉ ሁለት ቀን መካሄድ የለበትም በሚል ከቀናት በፊት የገባዉ የ4 ፓርቲዎች ቅሬታ ምርጫ ቦርድ ለወሰነዉ ዉሳኔ አስተዋፆ ማድረጉን ፓርቲዎቹ ገለጹ፡፡

የኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአጠቃላይ ምርጫ እና የአዲስ አበባ ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮች የምርጫ ቀን በሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ከወሰነበት ቀናት አንስቶ በርካታ ተቃዉሞዎች ተደምጠዋል፡፡ተቃዉሞ ካሰሙ አካላት መካከልም የተፎካካሪ ፓርቲዎች ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

ፓርቲዎች የአንድ ብሄር ተወላጆች ሁለት ጊዜ ይመርጣሉ፤ በህገወጥ መንገድም የነዋሪነት መታወቂያ እየታደለ በመሆኑ ችግሩን ያባብሰዋል የሚሉ ቅሬታዎችን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ቦርዱም በርካታ ዉይይቶችን ያደረገ ቢሆንም በዉሳኔዉ እንደጸናም ቆይቶ ነበር፡፡

ከቀናት በፊትም የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ፤ እናት፤ አብን ፤ መኢአድ ፓርቲዎች በጋር በመሆን ተቃዉሟቸዉን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቦርዱ ማስገባታቸዉን ገልጸዋል፡፡ይህ ደብዳቤም ባሳለፍነዉ ቅዳሜ ቦርዱ ለሻረዉ የሁለት ቀን የምርጫ ጉዳይ አስተዋጾ ማድረጉን የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የህዝብ ግንኑነት ሃለፊ ዶክተር በቃሉ አጥናፉ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡

የእናት ፓርቲ ለቀመንበር ዶክተር ሰይፈስላሴ አያለዉ በበኩላቸው በ4 ፓርቲዎች የገባዉ ቅሬታን ቦርዱ እንደ ባለድርሻ አካላት ተመልክቶን የወሰነዉ ነዉ ብለን እናምናለን ብለዋል፡፡ዉሳኔዉ ዘግይቷል በርካታ ዉይይቶች ከተደረጉ በኃላ ነዉ ቦርዱ የወሰነዉ በሚል በተለያዩ አካላት የሚነሱ ሃሳቦች  ቢኖሩም ዋና ጉዳያችን መሆን ያለበት ቀኑ ወደ አንድ ቀን መምጣቱ ነዉ ብለዋል፡፡

ዶክተር በቃሉ በበኩላቸዉ ቦርዱ የተለያዩ ማራዘሚያዎችን በተለያዩ ጊዚያት መወሰኑ ስራዎች ከአቅሙ በላይ እንደሆኑበት እና ሳያቅድ ዉሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ማሳያ ነዉ ብለዋል፡፡

ቀን 10/09/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post ምርጫዉ ሁለት ቀን መካሄድ የለበትም በሚል ከቀናት በፊት የገባዉ የ4 ፓርቲዎች ቅሬታ ምርጫ ቦርድ ለወሰነዉ ዉሳኔ አስተዋፆ ማድረጉን ፓርቲዎቹ ገለጹ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply